የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ ፌሌት፣ ዛዛ። እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።
የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ዮናታን፤ ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
ሶሳን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብጻዊ አገልጋይ ነበረው።