የአፋይም ወንድ ልጅ፤ ይሽዒ፣ ይሽዒም ሶሳን ወለደ። ሶሳን አሕላይን ወለደ።
የናዳብ ወንዶች ልጆች፤ ሴሌድ፣ አፋይም፤ ሴሌድ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ዮናታን፤ ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
የሺሞን ወንዶች ልጆች፤ አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት።
ከእነዚሁ ዐምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኰረብታማ አገር ወረሩ።