የናዳብ ወንዶች ልጆች፤ ሴሌድ፣ አፋይም፤ ሴሌድ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።
የአፋይም ወንድ ልጅ፤ ይሽዒ፣ ይሽዒም ሶሳን ወለደ። ሶሳን አሕላይን ወለደ።