Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ዘፍጥረት 39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ዮሴፍ በጲ​ጥ​ፋራ ቤት

1 ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ የመ​ጋ​ቢ​ዎ​ቹም አለቃ የሚ​ሆን የግ​ብፅ ሰው ጲጥ​ፋራ ወደ ግብፅ ከአ​ወ​ረ​ዱት ከይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እጅ ገዛው።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበር፤ ሥራ​ውም የተ​ከ​ና​ወ​ነ​ለት ሰው ሆነ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊው ጌታ​ውም ቤት ተሾመ።

3 ጌታ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዮ​ሴፍ ጋር እን​ዳለ፥ እርሱ የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ እን​ዲ​ያ​ከ​ና​ው​ን​ለት አየ።

4 ዮሴ​ፍም በጌ​ታው ፊት ሞገ​ስን አገኘ፤ እር​ሱ​ንም ደስ ያሰ​ኘው ነበር፤ በቤ​ቱም ላይ ሾመው፤ ያለ​ው​ንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።

5 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በቤቱ ባለ​ውም ሁሉ ላይ ከሾ​መው በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ፃ​ዊ​ውን ቤት በዮ​ሴፍ ምክ​ን​ያት ባረ​ከው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በረ​ከት በቤ​ቱም፥ በእ​ር​ሻ​ውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።

6 ያለ​ው​ንም ሁሉ ለዮ​ሴፍ በእጁ አስ​ረ​ከ​በው፤ ከሚ​በ​ላ​ውም እን​ጀራ በቀር ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው አል​ነ​በ​ረም። ዮሴ​ፍም መልኩ ያማረ፥ ፊቱም እጅግ የተ​ዋበ ነበር።

7 ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የጌ​ታው ሚስት በዮ​ሴፍ ላይ ዐይ​ን​ዋን ጣለ​ች​በት፤ “ከእ​ኔም ጋር ተኛ” አለ​ችው።

8 እር​ሱም እንቢ አለ፤ ለጌ​ታ​ውም ሚስት እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ ጌታዬ በቤቱ ያለ​ውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስ​ረ​ክ​ቦ​ኛል፤ በቤቱ ያለ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም፤

9 በዚህ ቤት ከእኔ የሚ​በ​ልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ​ሆ​ንሽ ከአ​ንቺ በቀር ያል​ሰ​ጠኝ ነገር የለም፤ እን​ዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደ​ር​ጋ​ለሁ? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ኀጢ​አ​ትን እሠ​ራ​ለሁ?”

10 ይህ​ንም ነገር በየ​ዕ​ለቱ ለዮ​ሴፍ ትነ​ግ​ረው ነበር፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር ይተኛ ዘንድ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ይሆን ዘንድ አል​ሰ​ማ​ትም።

11 በአ​ን​ዲ​ትም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ቀን ሥራ​ውን እን​ዲ​ሠራ ዮሴፍ ወደ ቤቱ ገባ፤ በቤ​ትም ውስጥ ከቤተ ሰዎች ማንም አል​ነ​በ​ረም።

12 ልብ​ሱን ይዛ፥ “ና ከእኔ ጋር ተኛ” አለ​ችው፤ እር​ሱም ልብ​ሱን በእ​ጅዋ ትቶ​ላት ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ።

13 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ልብ​ሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ በአ​የች ጊዜ፥

14 የቤ​ቷን ሰዎች ወደ እር​ስዋ ጠርታ እን​ዲህ ብላ ነገ​ረ​ቻ​ቸው፥ “እዩ፤ ይህ ዕብ​ራዊ ባርያ በእኛ እን​ዲ​ሣ​ለቅ አመ​ጣ​ብን፤ እርሱ ወደ እኔ ገብቶ ከእኔ ጋር ተኚ አለኝ፤ እኔም ድም​ፄን ከፍ አድ​ርጌ ጮኽሁ፤

15 ድም​ፄ​ንም ከፍ አድ​ርጌ እንደ ጮኽሁ ቢሰማ፥ ልብ​ሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ።”

16 ጌታው ወደ ቤቱ እስ​ኪ​ገባ ድረ​ስም ልብ​ሱን ከእ​ር​ስዋ ዘንድ አኖ​ረች።

17 ይህ​ንም ነገር እን​ዲህ ብላ ነገ​ረ​ችው፥ “ያመ​ጣ​ኸው ዕብ​ራ​ዊው ባሪያ ሊሣ​ለ​ቅ​ብኝ ወደ እኔ ገባ፤ ከአ​ን​ቺም ጋር ልተኛ አለኝ።

18 እኔም ድም​ፄን ከፍ አድ​ርጌ ስጮኽ ልብ​ሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ።”

19 ጌታ​ውም፥ “ባሪ​ያህ እን​ዲህ አደ​ረ​ገኝ” ብላ የነ​ገ​ረ​ች​ውን የሚ​ስ​ቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።

20 ዮሴ​ፍ​ንም ወሰ​ደው፤ የን​ጉሡ እስ​ረ​ኞች ወደ​ሚ​ታ​ሰ​ሩ​በት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገ​ባው፤ ከዚ​ያም በግ​ዞት ነበረ።

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አበ​ዛ​ለት፤ በግ​ዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገ​ስን ሰጠው።

22 የግ​ዞት ቤቱም አለቃ በግ​ዞት ያሉ​ትን እስ​ረ​ኞች ሁሉ በዮ​ሴፍ እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ በዚ​ያም የሚ​ደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ነበረ።

23 የግ​ዞት ቤቱ ጠባ​ቂ​ዎች አለ​ቃም በግ​ዞት ቤት የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ምንም አያ​ው​ቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮ​ሴፍ ትቶ​ለት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ረና፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ያቀ​ና​ለት ነበር።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች