Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 39:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ዮሴ​ፍ​ንም ወሰ​ደው፤ የን​ጉሡ እስ​ረ​ኞች ወደ​ሚ​ታ​ሰ​ሩ​በት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገ​ባው፤ ከዚ​ያም በግ​ዞት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ጌታውም ዮሴፍን ወስዶ፣ የንጉሥ እስረኞች ወደ ተጋዙበት እስር ቤት አስገባው። ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጌታውም ዮሴፍን ወስዶ፥ የንጉሥ እስረኞች ወደ ተጋዙበት እስር ቤት አስገባው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህ ዮሴፍን ወስዶ የንጉሡ እስረኞች ወዳሉበት እስር ቤት አስገባው። ነገር ግን ዮሴፍ በእስር ቤት በነበረበት ጊዜ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የዮሴፍም ጌታ ወሰደው የንጉሠ እስረኞችም ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤት አገባው፤ ከዚያም በግዞት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 39:20
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሌቦች በስ​ውር ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሀገር ሰር​ቀ​ው​ኛ​ልና፤ በዚ​ህም ደግሞ ምንም ያደ​ረ​ግ​ሁት ሳይ​ኖር በግ​ዞት ቤት አኑ​ረ​ው​ኛ​ልና።”


እነሆ፥ ዛሬ ጀመ​ርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ርቅ።


በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዷ​ልና ልደ​ቱን ማን ይና​ገ​ራል? ስለ ሕዝቤ ኀጢ​አት ለሞት ደረሰ።


አለ​ቆ​ችም በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ተቈ​ጥ​ተው መቱት፤ የግ​ዞት ቤት አድ​ር​ገ​ውት ነበ​ርና ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዮና​ታን ቤት ላኩት።


ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።


የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።


በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ሐዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች