Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 39:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጌታ​ውም፥ “ባሪ​ያህ እን​ዲህ አደ​ረ​ገኝ” ብላ የነ​ገ​ረ​ች​ውን የሚ​ስ​ቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጌታውም፣ “ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጌታውም “ባርያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ፥ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሚስቱ “የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቈጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጌታውም፦ ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ ብላ የነገረችውምን የሚስቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 39:19
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም ድም​ፄን ከፍ አድ​ርጌ ስጮኽ ልብ​ሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ።”


ለድ​ሃ​ዎች አባት ነበ​ርሁ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ሰው ክር​ክር መረ​መ​ርሁ።


ጻድ​ቃን እጃ​ቸ​ውን በዐ​መፃ እን​ዳ​ይ​ዘ​ረጉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኃ​ጥ​ኣ​ንን በትር በጻ​ድ​ቃን ዕጣ ላይ አይ​ተ​ው​ምና።


ከፍርድ በፊት ራሱን የሚከስስ ጻድቅ ነው፥ ያመጣው ባላጋራውም ይገሠጻል።


ብዙ ውኃ ፍቅ​ርን ያጠ​ፋት ዘንድ አይ​ች​ልም፥ ፈሳ​ሾ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​አ​ትም፤ ሰው የቤ​ቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ አይ​ን​ቁ​ትም።


እኔም፦ ተከ​ሳሹ በከ​ሳ​ሾቹ ፊት ሳይ​ቆም፥ ለተ​ከ​ሰ​ሰ​በ​ትም ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ፋንታ ሳያ​ገኝ ማንም ቢሆን አሳ​ልፎ መስ​ጠት የሮ​ማ​ው​ያን ሕግ አይ​ደ​ለም ብየ መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።


ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዐመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች