Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 39:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የጌ​ታው ሚስት በዮ​ሴፍ ላይ ዐይ​ን​ዋን ጣለ​ች​በት፤ “ከእ​ኔም ጋር ተኛ” አለ​ችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እያደርም የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዐይኗን ጣለች፤ አፍ አውጥታም፣ “ዐብረኸኝ ተኛ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እያደርም የጌታው ሚስት ዐይኗን ጣለችበት፤ አፍ አውጥታም፥ “አብረኸኝ ተኛ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስለ አፈቀረችው፥ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከዚህም በኍላ እንዲህ ሆነ የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይንዋን ጣለች፦ ከእኔም ጋር ተኛ አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 39:7
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይበ​ላም ዘንድ መብ​ሉን አቀ​ረ​በ​ች​ለት። እር​ሱም ያዛ​ትና፥ “እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔ ጋር ተኚ” አላት።


ምንዝር የሞላባቸው ኀጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።


ዝሙ​ትሽ ከሌ​ሎች ሴቶች ዝሙት ልዩ ነው፤ ማንም ለዝ​ሙት የሚ​ከ​ተ​ልሽ የለም፤ ዋጋ ሳይ​ሰ​ጥሽ አንቺ ዋጋ በመ​ስ​ጠ​ትሽ በዚህ ነገር ልዩ ሆነ​ሻል።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።


ከባ​ልዋ ገን​ዘብ ተቀ​ብላ የም​ታ​መ​ነ​ዝር ሴትን ትመ​ስ​ያ​ለሽ።


“ከዐ​ይኔ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፥ ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ሁም፤


በየ​መ​ን​ገዱ ራስ ከፍ ያለ​ውን ቦታ​ሽን ሠራሽ፤ ውበ​ት​ሽ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ ለመ​ን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ እግ​ር​ሽን ገለ​ጥሽ፤ ዝሙ​ት​ሽ​ንም አበ​ዛሽ።


ለጕ​ስ​ቍ​ል​ናሽ ከብ​ዙ​ዎች እረ​ኞች ጋር ኖርሽ የአ​መ​ን​ዝ​ራም ሴት ፊት ነበ​ረ​ብሽ፥ በሁ​ሉም ዘንድ ያለ ኀፍ​ረት ሄድሽ። ስለ​ዚህ የመ​ከ​ርና የበ​ልግ ዝናም ተከ​ለ​ከለ።


ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊቷም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦


ሕይወትህን ለሌላ እንዳትሰጥ፥ ንብረትህንም ምሕረት ለሌላቸው፤


ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


ልጄ ሆይ፥ ዝንጉዎች ሰዎች አያስቱህ፤ እሽም አትበላቸው።


የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራ ሴትም የተከበሩ ወንዶች ነፍስን ታጠምዳለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች