Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሰው ሁሉ በበ​ላይ ላሉ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ይገዛ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ል​ተ​ገኘ በቀር ሥል​ጣን የለ​ምና፤ ያሉ​ትም ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾሙ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ማንኛውም ሰው በሥልጣን ላሉት ሹማምት መገዛት ይገባዋል፤ ከእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣናት በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሁሉም ሰው ለበላይ ባለ ሥልጣናት ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ማንኛውም ሥልጣን የሚገኘው በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሆነና አሁን ያሉትም ባለሥልጣኖች የተሾሙት በእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ ሰው ሁሉ ለበላይ ባለሥልጣን መታዘዝ አለበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 13:1
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሥ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ምል ሁሉ ይከ​ብ​ራል፥ ዐመ​ፅን የሚ​ና​ገር አፍ ይዘ​ጋ​ልና።


ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


ቃሉ​ንም ተቀ​ብ​ለው ተጠ​መቁ፤ በዚ​ችም ዕለት ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ተጨ​መሩ።


ክፉ​ውን በመ​ል​ካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉ​ውን በክፉ ድል አት​ን​ሣው።


ለባ​ለ​ሥ​ል​ጣን አል​ገ​ዛም ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እንቢ ማለቱ ነው፤ መገ​ዛ​ትን እንቢ የሚ​ሉም በራ​ሳ​ቸው ላይ ቅጣ​ትን ያመ​ጣሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት ለባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ።


ማና​ቸ​ውም ሰው ቢኰራ፥ በአ​ም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለማ​ገ​ል​ገል የሚ​ቆ​መ​ውን ካህ​ኑን ወይም በዚያ ወራት ያለ​ውን ፈራ​ጁን ባይ​ሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ክፉ​ውን አስ​ወ​ግዱ፤


ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው።


እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ጌትነትንም ይጥላሉ፤ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ።


እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”


በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም አለው።


ችግ​ረ​ኛ​ውን ከመ​ሬት ያነ​ሣ​ዋል፤ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከጕ​ድፍ ያነ​ሣ​ዋል፤ ከሕ​ዝቡ መኳ​ን​ንት ጋር ያስ​ቀ​ም​ጠው ዘንድ፥ የክ​ብ​ር​ንም ዙፋን ያወ​ር​ሰው ዘንድ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች