Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ሮሜ 13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ስለ መታ​ዘዝ

1 ሰው ሁሉ በበ​ላይ ላሉ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ይገዛ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ል​ተ​ገኘ በቀር ሥል​ጣን የለ​ምና፤ ያሉ​ትም ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾሙ ናቸው።

2 ለባ​ለ​ሥ​ል​ጣን አል​ገ​ዛም ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እንቢ ማለቱ ነው፤ መገ​ዛ​ትን እንቢ የሚ​ሉም በራ​ሳ​ቸው ላይ ቅጣ​ትን ያመ​ጣሉ።

3 ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መል​ካም ለሚ​ሠራ የሚ​አ​ስ​ፈሩ አይ​ደ​ሉም፤ ሹሞ​ችን እን​ዳ​ት​ፈራ ብት​ፈ​ልግ መል​ካም አድ​ርግ፤ እነ​ርሱ ደግሞ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤

4 አንተ ሥራ​ህን ታሳ​ምር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ናቸ​ውና። ክፉ ብታ​ደ​ርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታ​ጠ​ቁም ለከ​ንቱ አይ​ደ​ለም፤ ክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን ለመ​ቅ​ጣት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸ​ውና።

5 ስለ​ዚህ ቍጣን ስለ መፍ​ራት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገ​ዛት ግድ ነው።

6 ስለ​ዚ​ህም ግብር ታገ​ቡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ለዚህ ሥራ የተ​ሾሙ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸ​ውና፤

7 ለሁ​ሉም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው አድ​ርጉ፤ ግብር ለሚ​ገ​ባው ግብ​ርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚ​ገ​ባው ቀረ​ጥን ስጡ፤ ዐሥ​ራት ለሚ​ገ​ባው ዐሥ​ራ​ትን ስጡ፤ ሊፈ​ሩት የሚ​ገ​ባ​ውን ፍሩ፤ ክብር የሚ​ገ​ባ​ው​ንም አክ​ብሩ።


ባል​ን​ጀ​ራን ስለ መው​ደድ

8 እርስ በር​ሳ​ችሁ ከመ​ዋ​ደድ በቀር ለማ​ንም ዕዳ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን የወ​ደደ ግን ሕግን ሁሉ ፈጸመ።

9 በኦ​ሪት እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ግ​ደል፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፥ አት​መኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእ​ዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁ​ሉም ራስ “ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው ነው።

10 ባል​ን​ጀ​ራ​ዉን የሚ​ወድ በባ​ል​ን​ጀ​ራዉ ላይ ክፉ ሥራ አይ​ሠ​ራም፤ ስለ​ዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።

11 ከእ​ን​ቅ​ልፍ የም​ት​ነ​ቁ​በት ጊዜ እንደ ደረሰ ዕወቁ፤ ካመ​ን​በት ጊዜ ይልቅ መዳ​ና​ችን ዛሬ ወደ እና ደር​ሳ​ለ​ችና።

12 ሌሊቱ አል​ፎ​አል፤ ቀኑም ቀር​ቦ​አል። እን​ግ​ዲህ የጨ​ለ​ማን ሥራ ከእና እና​ርቅ፤ የብ​ር​ሃ​ን​ንም ጋሻ ጦር እን​ል​በስ።

13 በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን።

14 ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ልበ​ሱት፤ የሥ​ጋ​ች​ሁ​ንም ምኞት አታ​ስቡ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች