Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 7:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ጽድቁ መጠን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም እዘ​ም​ራ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለ ጽድቁ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ፤ የልዑል እግዚአብሔርን ስም በመዝሙር አወድሳለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጉዳቱ በራሱ ይመለሳል፥ ዓመፃውም በአናቱ ላይ ትወርዳለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለ እውነተኛነቱ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ለልዑል አምላክ ስም የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 7:17
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኢ​ዮ​አብ ራስ ላይና በአ​ባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይም​ጣ​በት፤ በኢ​ዮ​አ​ብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ወይም ለም​ጻም ወይም አን​ካሳ ወይም በሰ​ይፍ የሚ​ወ​ድቅ ወይም እን​ጀራ የሌ​ለው ሰው አይ​ታጣ።”


አባቴ ዳዊት ሳያ​ውቅ ከእ​ርሱ የሚ​ሻ​ሉ​ትን ሁለ​ቱን ጻድ​ቃን ሰዎች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሠራ​ዊት አለቃ የኔ​ርን ልጅ አበ​ኔ​ርን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ሠራ​ዊት አለቃ የኢ​ያ​ቴ​ርን ልጅ አሜ​ሳ​ይን በሰ​ይፍ ገድ​ሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዐ​መፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።


ክብ​ርና ባለ​ጠ​ግ​ነት በቤቱ ነው፥ ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


እኔ ብቻ​ዬን እስ​ካ​ልፍ ድረስ ኃጥ​ኣን በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸው ይው​ደቁ።


ለተ​በ​ደ​ሉ​ትም የሚ​ፈ​ር​ድ​ላ​ቸው፥ ለተ​ራቡ ምግ​ብን የሚ​ሰጥ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​ሰ​ሩ​ትን ይፈ​ታ​ቸ​ዋል፤


በአ​ንተ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ት​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ምህ እዘ​ም​ራ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ፥ ክብ​ሩ​ንም ለበሰ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን ለበሰ፥ ታጠ​ቀም፤ ዓለ​ም​ንም እን​ዳ​ት​ና​ወጥ አጸ​ናት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ታላቅ ነው፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።


ነገር ግን ልዑል የሰው እጅ በሠ​ራው ቤት የሚ​ኖር አይ​ደ​ለም፤ ነቢይ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና።


ይህም የሆ​ነው፥ በሰ​ባው የይ​ሩ​በ​ኣል ልጆች ላይ የተ​ደ​ረ​ገው ዐመፅ እን​ዲ​መጣ፥ ደማ​ቸ​ውም በገ​ደ​ላ​ቸው በወ​ን​ድ​ማ​ቸው በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ላይ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም እን​ዲ​ገ​ድል እጆ​ቹን ባጸ​ኑ​አ​ቸው በሰ​ቂማ ሰዎች ላይ እን​ዲ​ሆን ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ቂ​ማን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራ​ሳ​ቸው ላይ መለ​ሰ​ባ​ቸው፤ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ የኢ​ዮ​አ​ታ​ምም ርግ​ማን ደረ​ሰ​ባ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች