Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጉዳቱ በራሱ ይመለሳል፥ ዓመፃውም በአናቱ ላይ ትወርዳለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለ ጽድቁ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀርባለሁ፤ የልዑል እግዚአብሔርን ስም በመዝሙር አወድሳለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለ እውነተኛነቱ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ለልዑል አምላክ ስም የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ጽድቁ መጠን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም እዘ​ም​ራ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 7:17
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ከኢዮአብ ቤት ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት፥ በምርኲዝ የሚሄድ አንካሳ፥ ወይም በሰይፍ ተመቶ የሚሞት ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ አይታጣ።”


አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ደም ጌታ ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የእስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር አዛዥ ዐማሣ ነበሩ።


ሥራው ምስጋናና ግርማ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።


የሚከብቡኝ ራሳቸውን አነሡ፥ የከንፈራቸው ክፋት ይክደናቸው።


የቸርነትህን ብዛት መታሰብ ያወጣሉ፥ በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ።


ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜም ምስጋናህን ይናገራል።


የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።


አቤቱ፥ በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።


በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር።


ኃጢአተኞች እንደ ሣር ቢበቅሉ ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ቢለመልሙ፥ ለዘለዓለም ዓለም እንደሚጠፉ ነው።


ጌታ ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ።


ነገር ግን ነቢዩ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ?’ ይላል ጌታ፥ ‘ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን?’ እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።


እግዚአብሔር ይህን ያደረገውም፥ በሰባው የይሩበኣል ልጆች ላይ ስለ ተፈጸመው ግፍና ስለ ፈሰሰው ደማቸው፥ ወንድማቸውን አቤሜሌክና ወንድሞቹን እንዲገድል የረዱትን የሴኬም ሰዎች ለመበቀል ነው።


በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰው፤ የይሩበኣል ልጅ የኢዮአታም ርግማን ደረሰባቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች