Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 31:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጻድ​ቃን ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ልባ​ች​ሁም የቀና ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ተመኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ፣ ለጎረቤቶቼ መዘባበቻ፣ ለወዳጆቼ መሣለቂያ ሆኛለሁ፤ መንገድ ላይ የሚያገኙኝም ይሸሹኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሕይወቴ በኅዘን አልቃለችና፥ ዓመታቴም በልቅሶ ጩኸት፥ ኃይሌ በችግር ደከመ፥ አጥንቶቼም ተነዋወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እኔ የጠላቶቼ መሳለቂያ፥ ለጐረቤቶቼ አስደንጋጭ፥ ለሚያውቁኝም አስፈሪ ነኝ፤ በመንገድ ሲያዩኝም ከእኔ ይሸሻሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 31:11
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምሕ​ረ​ትህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ ይከ​ተ​ለኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለረ​ዥም ዘመን እኖር ዘንድ።


በተ​ግ​ሣ​ጽህ ስለ ኀጢ​አቱ ሰውን ዘለ​ፍ​ኸው፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም እንደ ሸረ​ሪት አቀ​ለ​ጥ​ኻት፤ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከ​ንቱ ይታ​ወ​ካሉ።


ከተ​አ​ም​ራ​ትህ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ይደ​ን​ግ​ጣሉ፥ በም​ድር ዳር​ቻም የሚ​ኖሩ ይፈ​ራሉ፤ በጥ​ዋት ይወ​ጣሉ፥ ማታም ይደ​ሰ​ታሉ።


ረድ​ኤ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። ንጉ​ሣ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነውና።


አቤቱ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እው​ነ​ትም ይከ​ብ​ብ​ሃል።


ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”


ወን​ድ​ሞ​ች​ህና የአ​ባ​ትህ ቤት እነ​ርሱ ጭምር ክደ​ው​ሃ​ልና፥ ጮኸ​ውም በስ​ተ​ኋ​ላህ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በመ​ል​ካ​ምም ቢና​ገ​ሩህ አት​መ​ና​ቸው።


ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፥ ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ፥ ምራቲቱም በአማትዋ ላይ ትነሣለችና፥ የሰው ጠላቶች የቤቱ ሰዎች ናቸውና።


ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ነው፤” አለ። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።


በዚያን ጊዜ “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ራሱን ሊረግምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።


ክር​ስ​ቶ​ስም፥ “አን​ተን የነ​ቀ​ፉ​በት ነቀፋ በእኔ ላይ ደረሰ” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ለራሱ ያደላ አይ​ደ​ለም።


በፊተኛው ሙግቴ አንድ ስንኳ አልደረሰልኝም፤ ሁሉም ተዉኝ እንጂ፤ ይህንም አይቍጠርባቸው፤


የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።


አሁ​ንም ተግ​ዳ​ሮ​ቱን ተሸ​ክ​መን፥ ወደ እርሱ ወደ ከተ​ማው ውጭ እን​ውጣ።


ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች