Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 26:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አቤቱ መን​ገ​ድ​ህን አስ​ተ​ም​ረኝ፥ ስለ ጠላ​ቶ​ቼም በቀና መን​ገድ ምራኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እኔ ግን በተአማኒ ሕይወት እጓዛለሁ፤ አድነኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እኔ ግን በቅንነት ሄጃለሁ፥ አድነኝ ማረኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እኔ በበኩሌ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤ ምሕረትን አድርግልኝ፤ አድነኝም!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 26:11
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ አስ​በኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ወረ​ታ​ዬን አታ​ጥፋ።


ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ራሳ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ነጹ፥ መጥ​ተ​ውም በሮ​ቹን እን​ዲ​ጠ​ብቁ፥ የሰ​ን​በ​ት​ንም ቀን እን​ዲ​ቀ​ድሱ ነገ​ር​ኋ​ቸው። “አም​ላኬ ሆይ፥ ስለ​ዚህ ደግሞ አስ​በኝ፥ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ራራ​ልኝ” አልሁ።


በየ​ጊ​ዜ​ውም ዕን​ጨት ለሚ​ሸ​ከሙ ሰዎች ቍር​ባን፥ ለበ​ኵ​ራ​ቱም ሥር​ዐት አደ​ረ​ግሁ። “አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በመ​ል​ካም አስ​በኝ።”


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


አው​ስ​ጢድ በሚ​ባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።


በመ​ከ​ራዬ ቀን ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤ በጠ​ራ​ሁህ ቀን ፈጥ​ነህ ስማኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ራ​ል​ኛል፥ ያድ​ነ​ኛ​ልም፤ ምን ያስ​ፈ​ራ​ኛል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ይ​ወቴ መታ​መ​ኛዋ ነው፤ ምን ያስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ኛል?


በመ​ከ​ራህ ቀን ትጠ​ራ​ኛ​ለህ አድ​ን​ህ​ማ​ለሁ፥ አን​ተም ታከ​ብ​ረ​ኛ​ለህ።


ሕዝቤ፥ ስማኝ ልን​ገ​ርህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እመ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ፤ አም​ላ​ክስ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝ።


“አቤቱ፥ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በቅን ልብ እንደ ሄድሁ፥ በፊ​ት​ህም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አስብ።” ሕዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ ታላቅ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች