Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 20:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ታካች ሰው ሲያሽሟጥጡት አያፍርም፤ ስለዚህ በመከር ጊዜ ይለምናል፥ የሚሰጠውም የለም። በክምሩ እያለ ስንዴ የሚበደር እንደዚሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሰነፍ ሰው በወቅቱ አያርስም፤ ስለዚህ በመከር ወራት ይፈልጋል፤ አንዳችም አያገኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ታካች ሰው በብርድ ምክንያት አያርስም፥ ስለዚህ በመከር ይለምናል፥ ምንም አያገኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 መሬቱን በወቅቱ የማያርስ ሰነፍ ገበሬ በመከር ጊዜ የሚሰበስበው ምርት አይኖረውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 20:4
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል።


የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል። የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።


ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥ የማይሠራ ሰውም ይራባል።


ታካች ሰው እጁን በብብቱ ይሸሽጋል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።


ምክር በሰው ልብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።


ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ምንም ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።


ሁለትን ነገር ከአንተ እለምናለሁ፥ ሳልሞትም የሰጠኸኝን ጸጋህን አትከልክለኝ፤


አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገዱንም ተመልክተህ ቅና። ከእርሱም ይልቅ ብልህ ሁን።


ነፋ​ስን የሚ​ጠ​ባ​በቅ አይ​ዘ​ራም፥ ደመ​ና​ት​ንም የሚ​መ​ለ​ከት አያ​ጭ​ድም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች