Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 20:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሰው ክብሩ ከስድብ መከልከል ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ ቂል ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ማንኛውም ሞኝ ተቈጥቶ ጠብ ማነሣሣት ይችላል፤ ሰውን የሚያስከብረው ግን ከክርክር መራቅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 20:3
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።


የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ቸሮ​ችና ርኅ​ሩ​ኆች ሁኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ።


ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥ መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥


ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤


በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በአካላችሁ ክፍሎች ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን?


አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥ የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።


ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።


የችኩል፥ የነዝናዛና የነገረኛ ሰው ስሙ ቸነፈር ነው፥ ክፉን የሚያስብም ኃጥእ ነው።


ቍጡ ሰው ያለምክር ይሠራል፤ ብልህ ግን ብዙ ይታገሣል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊ​ባ​ኖስ ኵር​ን​ችት፦ ልጅ​ህን ለልጄ ሚስት አድ​ር​ገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊ​ባ​ኖ​ስም አውሬ አልፎ ኵር​ን​ች​ቱን ረገጠ።


በአ​ብ​ራ​ምና በሎጥ መን​ጎች ጠባ​ቆች መካ​ከ​ልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና ፌር​ዛ​ው​ያን በዚ​ያች ምድር ተቀ​ም​ጠው ነበር።


አብ​ራ​ምም ሎጥን አለው፥ “እኛ ወን​ድ​ማ​ማች ነንና በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በእ​ረ​ኞ​ቼና በእ​ረ​ኞ​ችህ መካ​ከል ጠብ አይ​ሁን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች