ምሳሌ 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 የንጉሥ ቍጣ ከአንበሳ ቍጣ አያንስም፤ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤ የሚያስቈጣውም ሰው ሕይወቱን ለመከራ ይዳርጋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የንጉሥ ቁጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 የንጉሥ ቊጣ እንደሚያገሣው አንበሳ ያስፈራል፤ የእርሱንም ቊጣ የሚያነሣሣ በራሱ ላይ የሞት ፍርድ እንደ ፈረደ ይቈጠራል። ምዕራፉን ተመልከት |