Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥ መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጥበብ ሰውን ታጋሽ ታደርገዋለች፤ በደልን ንቆ መተውም መከበሪያው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፥ ለበደለኛውም ይቅር ይል ዘንድ ክብር ይሆንለታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የቊጣን ስሜት መቈጣጠር አስተዋይነት ነው፤ ለበደለም ይቅርታ ማድረግ ጨዋነት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 19:11
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የደ​ማ​ስቆ ወን​ዞች ባብ​ናና ፋርፋ ከእ​ስ​ራ​ኤል ውኆች ሁሉ አይ​ሻ​ሉ​ምን? ሄጄስ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ መጠ​መ​ቅና መን​ጻት አይ​ቻ​ለ​ኝም ኖሮ​አ​ልን?” ብሎ በቍጣ ተመ​ልሶ ሄደ።


ሁለት ምላስ የሆነ ሰው የጉባኤን ምሥጢር ይገልጣል፤ በአንደበቱ የታመነ ግን ነገርን ይሰውራል።


ሰነፍ ቍጣውን በየቀኑ ይናገራል፤ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።


ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤


ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን የሆነውን ስንኳ ያጠፋል። ትዕግሥተኛ ሰው ክርክርን ያጠፋል፥ ኀጢአተኛ ሰው ግን ጠብን ፈጽሞ ያነሣል።


ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።


የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።


ጠላቴን እበቀለዋለሁ አትበል፤ ነገር ግን እንዲረዳህ እግዚአብሔርን ተማመን።


የሰው ክብሩ ከስድብ መከልከል ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ቸሮ​ችና ርኅ​ሩ​ኆች ሁኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች