Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ለአላዋቂ ቅምጥልነት አይገባውም፥ አገልጋይም ከስድብ ጋር ቢገዛ ይበረታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሞኝ ተንደላቅቆ መኖር አይገባውም፤ ባሪያ የመሳፍንት ገዥ ከሆነማ የቱን ያህል ይከፋ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለሰነፍ ቅምጥልነት አይገባውም፥ ይልቁንም ባርያ በአለቆች ላይ ይገዛ ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሞኞች በድሎት መኖር አይችሉም፤ የባሪያ በመኳንንት ላይ ገዢ መሆንማ ምንኛ የከፋ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 19:10
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።


የታመነች ከንፈር ለሰነፍ፥ የሐሰት ከንፈርም ለጻድቅ አትስማማውም።


ሕዝብ በሕ​ዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይገ​ፋ​ፋል፤ ብላ​ቴ​ና​ውም በሽ​ማ​ግ​ሌው ላይ፥ የተ​ጠ​ቃ​ውም በከ​በ​ር​ቴው ላይ ይታ​በ​ያል።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! ከአ​ም​ላ​ክህ ርቀህ አመ​ን​ዝ​ረ​ሃ​ልና እንደ አሕ​ዛብ ደስ አይ​በ​ልህ፤ ሐሴ​ት​ንም አታ​ድ​ርግ፤ ከእ​ህ​ሉና ከወ​ይኑ አው​ድማ ሁሉ ይልቅ የግ​ል​ሙ​ትና ዋጋን ወድ​ደ​ሃል።


“አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር።


በሲ​ኦ​ልም በሥ​ቃይ ሳለ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ አብ​ር​ሃ​ምን ከሩቅ አየው፤ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጦ አየው።


ተጨነቁና እዘኑ፤ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ሐዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።


አቤ​ግ​ያም ወደ ናባል መጣች፤ እነ​ሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደ​ርግ ነበር፤ ናባ​ልም እጅግ ሰክሮ ነበ​ርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች