Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሞኝ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የሰነፍ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሩም ለነፍሱ ወጥመድ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሞኝ በሚናገርበት ጊዜ ራሱን በጒዳት ላይ ይጥላል፤ አነጋገሩም ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 18:7
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሰ​ወ​ሩ​ብኝ ወጥ​መድ፥ ዐመ​ፃ​ንም ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች እን​ቅ​ፋት ጠብ​ቀኝ።


ከተ​አ​ም​ራ​ትህ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ይደ​ን​ግ​ጣሉ፥ በም​ድር ዳር​ቻም የሚ​ኖሩ ይፈ​ራሉ፤ በጥ​ዋት ይወ​ጣሉ፥ ማታም ይደ​ሰ​ታሉ።


ጠቢብ ዕውቀትን ይሸሽጋል፤ የችኩል አፍ ግን ለጥፋት ይቀርባል።


በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፤ በከንፈሩ የማይታገሥ ግን በመሰናክል ይወድቃል።


ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።


አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።


ከሰነፎች አፍ የስድብ በትር ይወጣል፤ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።


በጎ ዐሳብ ገንዘብ ላደረጋት ሰው የሕይወት ምንጭ ናት፤ የሰነፎች ትምህርት ግን ክፉ ናት።


ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥ የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል።


ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ ሁሉም በኀጢአቱ ልባብ ይታሰራል።


የሰው ከንፈሩ ጽኑ ወጥመድ ነው፤ በአፉ ቃል ይጠፋል።


እር​ስ​ዋ​ንም ባየ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ወዮ​ልኝ ልጄ ሆይ! ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፌን ከፍ​ቻ​ለ​ሁና፥ ከዚ​ያ​ውም እመ​ለስ ዘንድ አል​ች​ል​ምና አሰ​ና​ከ​ል​ሽኝ፤ አስ​ጨ​ነ​ቅ​ሽ​ኝም” አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች