Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 18:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከወዳጆቹ መለየትን የሚወድድ ሰው ምክንያትን ይፈልጋል፥ ሁልጊዜም ለሽሙጥ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ ቅን የሆነውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ራስ ወዳድ ሰው የራሱን ምኞት ብቻ ይከተላል፤ ከሌላ ሰው የሚቀርብ ትክክለኛ አስተሳሰብን እንኳ ይቃወማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 18:1
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በም​ድ​ርም ከአ​ለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝ​ብህ ተለ​ይ​ተን እን​ከ​ብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካል​ሄ​ድህ፥ እኔና ሕዝ​ብህ በአ​ንተ ዘንድ በእ​ው​ነት ሞገስ ማግ​ኘ​ታ​ችን በምን ይታ​ወ​ቃል?” አለው።


የዐዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ኀዘን ነው፤ ደስ ባለውም ጊዜ ከጥል ጋር ግንኙነት የለውም።


የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።


ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፤ በከንፈሩ የሚያባብል ሰውን አትገናኘው።


የሰው ክብሩ ከስድብ መከልከል ነው፤ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።


ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል።


ልጄ ሆይ፥ ቸል አትበል ዐሳቤንና ምክሬን ጠብቅ፤


ምክርና ሥልጣን የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል የእኔ ነው፥ ብርታትም የእኔ ነው።


በዋ​ዘ​ኞች ጉባኤ አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁም፤ ነገር ግን በእ​ጅህ ፊት ፈር​ቻ​ለሁ፤ ምሬ​ትን ሞል​ተ​ህ​ብ​ኛ​ልና ለብ​ቻዬ ተቀ​መ​ጥሁ።


ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።


እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፤ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።


ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።


እንዲህም አላቸው “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ ‘አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፤ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፤ እንዳይመለሱ ኀጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው’ ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወን​ጌል ለማ​ስ​ተ​ማር ተለ​ይቶ ከተ​ጠራ ሐዋ​ርያ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ከሚ​ሆን ከጳ​ው​ሎስ፥


ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ከእ​ን​ስ​ሶች ሰኰ​ናው የተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀ​ውን፥ ጥፍ​ሩም ከሁ​ለት የተ​ከ​ፈ​ለ​ውን፥ የሚ​ያ​መ​ሰ​ኳ​ው​ንም እን​ስሳ ሁሉ ትበ​ላ​ለህ።


እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች