Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 18:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 መለየት የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ ቅን የሆነውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ራስ ወዳድ ሰው የራሱን ምኞት ብቻ ይከተላል፤ ከሌላ ሰው የሚቀርብ ትክክለኛ አስተሳሰብን እንኳ ይቃወማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከወዳጆቹ መለየትን የሚወድድ ሰው ምክንያትን ይፈልጋል፥ ሁልጊዜም ለሽሙጥ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 18:1
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።


በዋዘኞች ጉባኤ አልተቀመጥኩም አልተደሰትኩምም፤ ቁጣን ሞልተህብኛልና እጅህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።


ልጄ ሆይ፥ ጌታንና ንጉሥን ፍራ፥ ከዓመፀኞችም ጋር አትደባለቅ።


እነዚህ መለያየትን የሚፈጥሩ ፍጥረታውያን የሆኑ፥ መንፈስም የሌላቸው ናቸው።


ማለዳም ገና ጎሕ ሳይቀድ፥ ኢየሱስ ተነሥቶ ከቤት ወጣ፤ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራም ሄዶ ይጸልይ ጀመር።


የራሱን ኀዘን ልብ ያውቃል፥ ከደስታውም ጋር ሌላ ሰው አይገናኝም።


“መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው በእርሻ ውስጥ አግኝቶ መልሶ የሸሸገው የተሰወረ መዝገብ ትመስላለች፤ ከደስታውም ብዛት ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ ያንን እርሻ ገዛው።


በማይመለከተው ገብቶ የሚሟገት፥ ውሻን በጆሮው እንደሚይዝ ነው።


እኔና ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? እኔና ሕዝብህ በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ የተለየን የምንሆነው አንተ ከእኛ ጋር በመውጣትህ አይደለምን?”


ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ሰውን አትገናኘው።


የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፥ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።


የክርስቶስ ኢየሱስ ባርያ ጳውሎስ፥ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል የተለየ፥


እርሱም፥ “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቷአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን ሁሉ ነገር በምሳሌ ይነገራቸዋል፤


እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


ስለዚህም ጌታ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፤ ርኩስንም አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥


ለሠራዊት ጌታ ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መጾምና ማልቀስ ይገባኛልን?” ብለው እንዲናገሩ ልኳቸው ነበር።


ልጄ ሆይ፥ እነዚህ ከዐይኖችህ አይራቁ፥ መልካም ጥበብንና ጥንቃቄን ጠብቅ።


ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው፥ ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ።


ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፥ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች