Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 23:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በለ​ዓ​ምን ተገ​ና​ኘው፤ ቃል​ንም በአፉ አኖረ፥ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በለው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር በለዓምን ተገናኘው፤ በአፉም መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና ይህን መልእክት ንገረው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታም በለዓምን አገኘው፥ ቃልንም በአፉ አድርጎ፦ “ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም ተናገር” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔርም በለዓምን በዚያ ተገናኘው፤ የሚናገረውንም መልእክት ሰጥቶ ወደ ባላቅ ተመልሰህ እንዲህ በለው አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እግዚአብሔርም በለዓምን ተገናኘ፥ ቃልንም በአፉ አድርጎ፦ ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም በል አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 23:16
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ በለ​ዓም በሌ​ሊት መጥቶ፥ “ሰዎቹ ይጠ​ሩህ ዘንድ መጥ​ተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ታደ​ር​ጋ​ለህ” አለው።


የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን አለው፥ “በዚህ በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ።”


ወደ እር​ሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የሞ​ዓብ አለ​ቆች በመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አለ?”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ለ​ዓም አፍ ቃልን አኖረ፤ “ወደ ባላቅ ተመ​ለስ፤ እን​ዲ​ህም በል” አለው።


በለ​ዓ​ምም እስ​ራ​ኤ​ልን መባ​ረክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካም እንደ ሆነ ባየ ጊዜ፥ እንደ ልማዱ ለማ​ሟ​ረት ወደ ፊት አል​ሄ​ደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን መለሰ።


ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቃሌ​ንም በአፉ አኖ​ራ​ለሁ፤ እንደ አዘ​ዝ​ሁ​ትም ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች