Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 23:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ባላ​ቅም፥ “በዚያ እነ​ር​ሱን ወደ​ማ​ታ​ይ​በት ወደ ሌላ ቦታ እባ​ክህ፥ ከእኔ ጋር ና፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ወገን ብቻ ታያ​ለህ፤ ሁሉን ግን አታ​ይም፤ በዚ​ያም እነ​ር​ሱን ርገ​ም​ልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚህ በኋላ ባላቅ፣ “እነርሱን ማየት ወደምትችልበት ወደ ሌላ ቦታ እንሂድ፤ በእዚያም ሁሉን ሳይሆን በከፊል ብቻ ታያቸዋለህ፤ እዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ባላቅም እንዲህ አለው፦ “በዚያ ሆነህ እንድታያቸው፥ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ና፤ ዳርቻቸውንም ብቻ ታያለህ፥ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ባላቅም በለዓምን “ከእስራኤላውያን ሁሉን ሳይሆን ጥቂቱን ብቻ ወደምታይበት ወደ ሌላ ቦታ ከእኔ ጋር እንሂድ፤ በዚያ ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ባላቅም፦ በዚያ ሆነህ ታያቸው ዘንድ፥ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ና፤ ዳርቻቸውንም ብቻ ታያለህ፥ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 23:13
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ቅጥር አጠ​ገብ ኤል​ዛ​ቤ​ልን ውሾች ይበ​ሉ​አ​ታል፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ አክዓብ ወደ ባሪ​ያው ወደ ኤል​ያስ መጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፦


ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።


በነ​ጋ​ውም ባላቅ በለ​ዓ​ምን ይዞ ወደ በአል ኮረ​ብታ አወ​ጣው፤ በዚ​ያም ሆኖ የሕ​ዝ​ቡን አንድ ወገን አሳ​የው።


እነ​ሆም፥ የም​ድ​ሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአ​ቅ​ራ​ቢ​ያ​ች​ንም ተቀ​ም​ጦ​አል፤ አሁ​ንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበ​ል​ጣ​ልና ልወ​ጋ​ቸ​ውና ከም​ድ​ሪቱ ላሳ​ድ​ዳ​ቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገ​ም​ልኝ፤ አንተ የመ​ረ​ቅ​ኸው ምሩቅ፥ የረ​ገ​ም​ኸ​ውም ርጉም እንደ ሆነ አው​ቃ​ለ​ሁና” ብሎ ይጠ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን መልሶ፥ “በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፌ ያደ​ረ​ገ​ውን እና​ገር ዘንድ የም​ጠ​ነ​ቀቅ አይ​ደ​ለ​ምን?”


በሜዳ ወደ ተገ​ነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰ​ደው፤ አዞ​ረ​ውም፤ ሰባ​ትም መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሠራ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈን፥ አን​ድም አውራ በግ አሳ​ረገ።


የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ የሴ​ፎር ልጅ ባላቅ ተነ​ሥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጋ፤ እን​ዲ​ረ​ግ​ማ​ች​ሁም የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ምን ልኮ አስ​ጠ​ራው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች