Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ “ወደ መካ​ከ​ላ​ቸው እስ​ክ​ን​መ​ጣና እስ​ክ​ን​ገ​ድ​ላ​ቸው ድረስ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም እስ​ክ​ና​ስ​ተ​ጓ​ጕል ድረስ አያ​ው​ቁም፤ አያ​ዩም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጠላቶቻችን ደግሞ፣ “በመካከላቸው ገብተን እስክንገድላቸውና ሥራውን እስክናስቆም ድረስ አያውቁም ወይም አያዩም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ቅጥሩን የሚሠሩትና ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ፥ በአንድ እጃቸው ደግሞ የጦር መሣሪያ ይይዙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ጠላቶቻችን የምናደርገውን ከማወቃቸውና ከማየታቸው በፊት በመካከላቸው ተገኝተን እነርሱን ገድለን ሥራቸውንም እናቆመዋለን” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጠላቶቻችንም፦ ወደ መካከላቸው እስክንመጣና እስክንገድላቸው ድረስ ሥራቸውንም እስክናስተጓጉል ድረስ አያውቁምና አያዩም አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 4:11
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደክ​ሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወ​ድ​ቅ​በ​ታ​ለሁ፤ አስ​ፈ​ራ​ው​ማ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸ​ሻል፤ ንጉ​ሡ​ንም ብቻ​ውን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ፤


ይሁ​ዳም፥ “የተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎች ኀይል ደከመ፤ ፍር​ስ​ራ​ሹም ብዙ ነው፤ ቅጥ​ሩ​ንም እን​ሠራ ዘንድ አን​ች​ልም” አሉ።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የተ​ቀ​መ​ጡት አይ​ሁድ መጥ​ተው፥ “ከስ​ፍ​ራው ሁሉ ይመ​ጡ​ብ​ናል ብለው ዐሥር ጊዜ ነገ​ሩን።”


እኛም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ጸለ​ይን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ነሣ በአ​ን​ጻ​ራ​ቸው ተጠ​ባ​ባ​ቂ​ዎ​ችን በሌ​ሊ​ትና በቀን አደ​ረ​ግን።


ለእ​ግ​ሮቼ ወጥ​መ​ድን አዘ​ጋጁ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም አጐ​በ​ጡ​አት፤ ጕድ​ጓ​ድን በፊቴ ቈፈሩ፥ በው​ስ​ጡም ወደቁ።


ስለ​ዚህ ምክ​ን​ያት ጥፋት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ጥል​ቀ​ቱን አታ​ው​ቂም፤ በው​ስ​ጡም ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ጕስ​ቁ​ልና ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ማም​ለ​ጥም አይ​ቻ​ል​ሽም፤ ሞት ድን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ አታ​ው​ቂ​ምም።


በነ​ጋም ጊዜ አይ​ሁድ ተሰ​ብ​ስ​በው፥ ጳው​ሎ​ስን እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ ተስ​ማ​ም​ተው ተማ​ማሉ።


አንተ ግን እሽ አት​በ​ላ​ቸው፤ ሊገ​ድ​ሉት ሽም​ቀ​ዋ​ልና፤ እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉ​ትም ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ እን​ዲህ የተ​ማ​ማሉ ሰዎች ከአ​ርባ ይበ​ዛሉ፤ አሁ​ንም እስ​ክ​ት​ል​ክ​ላ​ቸው ይጠ​ብ​ቃሉ እንጂ እነ​ርሱ ቈር​ጠ​ዋል።”


የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች