Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይሁ​ዳም፥ “የተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎች ኀይል ደከመ፤ ፍር​ስ​ራ​ሹም ብዙ ነው፤ ቅጥ​ሩ​ንም እን​ሠራ ዘንድ አን​ች​ልም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ፣ “የሠራተኞቹ ጕልበት እየደከመ ነው፤ ከፍርስራሹም ብዛት የተነሣ ቅጥሩን መልሰን ለመሥራት አንችልም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከዚያን ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ጎልማሶች ሥራ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ ጋሻ፥ ጦር፥ ቀስትና ጥሩር ይይዙ ነበር፤ ሹማምቱም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሰዎች “የሸክም ሥራ እያደከመን ሄደ፤ ገና መነሣት ያለበት ፍርስራሽ ብዙ ነው፤ ቅጽሩን እንሠራ ዘንድ አንችልም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይሁዳም፦ የተሸካሚዎች ኃይል ደከመ፥ ፍርስራሹም ብዙ ነው፥ ቅጥሩንም እንሠራ ዘንድ አንችልም አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 4:10
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሰባ ሺህ፥ በተ​ራ​ሮ​ቹም ላይ የሚ​ጠ​ር​ቡ​ትን ሰማ​ንያ ሺህ፥ በሕ​ዝ​ቡም ሥራ ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ሦስት ሺህ ስድ​ስት መቶ አደ​ረገ።


በተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎ​ችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚ​ሠሩ ላይ ተሾ​መው ነበር፤ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቹና አለ​ቆ​ቹም በረ​ኞ​ቹም ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ነበሩ።


ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ “ወደ መካ​ከ​ላ​ቸው እስ​ክ​ን​መ​ጣና እስ​ክ​ን​ገ​ድ​ላ​ቸው ድረስ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም እስ​ክ​ና​ስ​ተ​ጓ​ጕል ድረስ አያ​ው​ቁም፤ አያ​ዩም” አሉ።


በወ​ን​ድ​ሞ​ቹና በሰ​ማ​ርያ ሠራ​ዊ​ትም ፊት፥ “ከተ​ማ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ እነ​ዚህ ደካ​ሞች አይ​ሁድ ኀይ​ላ​ቸው ምን​ድን ነው? ይተ​ዉ​ላ​ቸ​ዋ​ልን? ይሠ​ዋ​ሉን? በአ​ንድ ቀንስ ይጨ​ር​ሳ​ሉን? የተ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንስ ድን​ጋይ ከፍ​ር​ስ​ራሹ መል​ሰው ያድ​ኑ​ታ​ልን?” ብሎ ተና​ገረ።


እኛም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ጸለ​ይን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ነሣ በአ​ን​ጻ​ራ​ቸው ተጠ​ባ​ባ​ቂ​ዎ​ችን በሌ​ሊ​ትና በቀን አደ​ረ​ግን።


“የሰው ልጅ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሠራ​ዊ​ቱን በጢ​ሮስ ላይ ጽኑ ሥራን አሠ​ራ​ቸው፤ ራስ ሁሉ የተ​ላጨ፥ ጫን​ቃም ሁሉ የተ​ላጠ ሆኖ​አል፤ ነገር ግን በላ​ይዋ ስለ አሠ​ራው ሥራ እር​ሱና ሠራ​ዊቱ ከጢ​ሮስ ደመ​ወዝ አል​ተ​ቀ​በ​ሉም።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ይህ ሕዝብ፦ ዘመኑ አልደረሰም፥ የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ዘመን አልደረሰም ይላል ብሎ ተናገረ።


ከእ​ርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀ​ይል ከእኛ ይበ​ረ​ታ​ሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መው​ጣት አን​ች​ልም” አሉ።


ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች