Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 4:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከፈ​ረ​ሰ​ኞ​ችና ከቀ​ስ​ተ​ኞች ድምፅ የተ​ነሣ ሀገሯ ሁሉ ሸሽ​ታ​ለች፤ ወደ ዋሻ​ዎች ይገ​ባሉ፥ በዛፍ ሥር ተሸ​ሸጉ፥ በቋ​ጥ​ኝም ላይ ይወ​ጣሉ፤ ከተ​ማዋ ሁሉ ተለ​ቅ​ቃ​ለች፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ሰው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጩኸት የተነሣ፣ ከተማ ሁሉ ይሸሻል፤ አንዳንዶች ደን ውስጥ ይገባሉ፤ ሌሎችም ቋጥኝ ላይ ይወጣሉ፤ ከተሞች ሁሉ ባዶ ቀርተዋል፤ የሚኖርባቸውም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ከፈረሰኛና ከቀስተኛ ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ትሸሻለች፤ ጥቅጥቅ ወዳለ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፤ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ከፈረሰኞችና ከቀስት ወርዋሪዎች ድንፋታ የተነሣ፥ የከተማ ሰው ሁሉ ይሸሻል፤ አንዳንዶቹ ወደ ጫካ ይሮጣሉ፤ የቀሩት በየአለቱ ላይ ይወጣሉ፤ እያንዳንዱ ከተማ ሰው የማይኖርበት ወና ይሆናል፤ የሚኖርበትም አያገኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ሸሽታለች፥ ወደ ችፍግ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፥ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 4:29
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ሠራ​ዊት አለ​ቆች አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ምና​ሴ​ንም በዛ​ን​ጅር ያዙት፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዱት።


ከአ​ንድ ሰው ዛቻ የተ​ነሣ ሺህ ሰዎች ይሸ​ሻሉ፤ እና​ን​ተም በተ​ራራ ራስ ላይ እን​ዳለ ምሰሶ፥ በኮ​ረ​ብ​ታም ላይ እን​ዳለ ምል​ክት ሆና​ችሁ እስ​ክ​ት​ቀሩ ድረስ፥ ከአ​ም​ስት ሰዎች ዛቻ የተ​ነሣ ብዙ​ዎች ይሸ​ሻሉ።”


ከዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዎ​ችን ያር​ቃል፤ በም​ድ​ርም የቀ​ሩት ይበ​ዛሉ።


“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችን እል​ካ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ያጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ዋል፤ ከዚ​ያም በኋላ ብዙ አድ​ዳ​ኞ​ችን እል​ካ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ከየ​ተ​ራ​ራ​ውና ከየ​ኮ​ረ​ብ​ታው ሁሉ ከየ​ድ​ን​ጋ​ዩም ስን​ጣቂ ውስጥ ያድ​ድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል።


አን​በሳ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ቶ​አል፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው የሚ​ዘ​ርፍ ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ምድ​ር​ሽን ባድማ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ሽ​ንም ሰው እን​ዳ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ያፈ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ ከስ​ፍ​ራው ወጥ​ቶ​አል።


ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ ሸሹ፤ በሁ​ለ​ቱም ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሥ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ። ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ሄዱ።


ቀስ​ት​ንና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተ​ም​ማል፤ በሰ​ረ​ገ​ላና በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠ​ፉ​ሻል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ሠ​ው​ያው ላይ ቆሞ አየ​ሁት፤ እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “አበ​ቦች የተ​ሳ​ሉ​ባ​ቸ​ውን ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ምታ፤ መድ​ረ​ኮ​ቹም ይና​ወ​ጣሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ቍረጥ፤ እኔም ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ሩ​ትን በሰ​ይፍ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ ከሚ​ሸ​ሹ​ትም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጡ​ትም የሚ​ድን የለም።


ያን​ጊ​ዜም ተራ​ሮ​ችን ‘በላ​ያ​ችን ውደቁ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ሰው​ሩን’ ይሉ​አ​ቸ​ዋል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ወደ እነ​ርሱ መሄድ እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋ​ሻና በግ​ንብ፥ በገ​ደ​ልና በቋ​ጥኝ፥ በጕ​ድ​ጓ​ድም ውስጥ ተሸ​ሸጉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች