ኤርምያስ 4:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ከፈረሰኛና ከቀስተኛ ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ትሸሻለች፤ ጥቅጥቅ ወዳለ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፤ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጩኸት የተነሣ፣ ከተማ ሁሉ ይሸሻል፤ አንዳንዶች ደን ውስጥ ይገባሉ፤ ሌሎችም ቋጥኝ ላይ ይወጣሉ፤ ከተሞች ሁሉ ባዶ ቀርተዋል፤ የሚኖርባቸውም የለም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ከፈረሰኞችና ከቀስት ወርዋሪዎች ድንፋታ የተነሣ፥ የከተማ ሰው ሁሉ ይሸሻል፤ አንዳንዶቹ ወደ ጫካ ይሮጣሉ፤ የቀሩት በየአለቱ ላይ ይወጣሉ፤ እያንዳንዱ ከተማ ሰው የማይኖርበት ወና ይሆናል፤ የሚኖርበትም አያገኝም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ሀገሯ ሁሉ ሸሽታለች፤ ወደ ዋሻዎች ይገባሉ፥ በዛፍ ሥር ተሸሸጉ፥ በቋጥኝም ላይ ይወጣሉ፤ ከተማዋ ሁሉ ተለቅቃለች፤ የሚቀመጥባትም ሰው የለም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ሸሽታለች፥ ወደ ችፍግ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፥ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም። ምዕራፉን ተመልከት |