ኤርምያስ 31:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ሂዱ፦ እስራኤልንም አታጥፉ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ፣ በምድረ በዳ ሞገስን ያገኛል፤ እኔም ለእስራኤል ዕረፍት ለመስጠት እመጣለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ጌታ እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ማረፊያ ሊሻ በሄደ ጊዜ ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እስራኤል ዕረፍትን ለማግኘት ወደ ፊት በመጣ ጊዜ ከጦርነት የተረፉት በምድረ በዳ የእኔን የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኛሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ማረፊያ ሊሻ በሄደ ጊዜ ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ምዕራፉን ተመልከት |