Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሁሉም ሰው ጅልና ዕውቀት የለሽ ነው። የወርቅ አንጥረኛው ሁሉ በሠራው ጣዖት ዐፍሯል፤ የቀረጻቸው ምስሎቹ የሐሰት ናቸው፤ እስትንፋስም የላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሰው ሁሉ ቂላ ቂልና እውቀት የሌለው ሆኖአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሁሉም ሞኞችና አላዋቂዎች ሆኑ፤ የሠሩአቸው ምስሎች ሐሰተኞች ስለ ሆኑና ሕይወትም ስለሌላቸው አንጥረኛው በሠራቸው ጣዖቶች አፍሮባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሰው ሁሉ እውቀት አጥቶ ሰንፎአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፥ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 10:14
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በቅ​ን​ነት የሚ​ሄድ፥ ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም እው​ነ​ትን የሚ​ና​ገር።


በም​ድረ በዳ እንደ ተፈ​ታ​ተ​ኑ​ትና እን​ዳ​ስ​ቈ​ጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድም​ፁን ብት​ሰሙ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ።


ባሕር በሞ​ላዋ፥ ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይና​ወጡ።


በተ​ቀ​ረ​ጹ​ትም ምስ​ሎች የሚ​ታ​መኑ፥ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፈጽ​መ​ውም ያፍ​ራሉ።


ከሰ​ዎች መካ​ከል ደን​ቆ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሰ​ብ​ሰቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቁሙ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም።


የሚ​ቃ​ወ​ሙት ሁሉም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ አፍ​ረ​ውም ይሄ​ዳሉ።


እን​ግ​ዲህ እኔ ጽድ​ቄ​ንና የማ​ይ​ረ​ባ​ሽን የአ​ን​ቺን በደል እና​ገ​ራ​ለሁ።


እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”


በአ​ንድ ጊዜ ሰን​ፈ​ዋል፥ ደን​ቍ​ረ​ው​ማል፤ ጣዖ​ታት የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩት የእ​ን​ጨት ነገር ብቻ ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እው​ነት ሐሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ታ​ልና፤ ተዋ​ር​ደ​ውም ፍጥ​ረ​ቱን አም​ል​ከ​ዋ​ልና፤ ሁሉን የፈ​ጠ​ረ​ውን ግን ተዉት፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ ነው፤ አሜን።


በነ​ጋ​ውም ማለዱ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳ​ጎ​ንም ራስ፥ ሁለቱ እጆ​ቹም ተቈ​ር​ጠው እየ​ራ​ሳ​ቸው በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው ነበር፤ ሁለቱ መሀል እጆ​ቹም በወ​ለሉ ላይ ወድ​ቀው ነበር። የዳ​ጎ​ንም ደረት ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች