Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባ​ዙም፤ የባ​ሕ​ር​ንም ውኃ ሙሉ​አት፤ ወፎ​ችም በም​ድር ላይ ይብዙ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እግዚእብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፥ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር “ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ የባሕርን ውሃ ይሙላ፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እግዚእብሔርም እንድህ ብሎ ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኂ ሙሉአት ውፎችም በምድር ላይ ይብዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:22
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላቅ አን​በ​ሪ​ዎ​ችን፥ ውኃ ያስ​ገ​ኘ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሕያው ፍጥ​ረ​ትን ሁሉ በየ​ወ​ገኑ፥ የሚ​በ​ርሩ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ፈጠረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።


ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አም​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም፤ የባ​ሕ​ርን ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሳ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ግዙ​አ​ቸው።”


ላባም፥ “በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገ​ስን የማ​ገኝ ብሆ​ንስ ከዚሁ ተቀ​መጥ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንተ ምክ​ን​ያት እንደ ባረ​ከኝ ተመ​ል​ክ​ቼ​አ​ለ​ሁና።


አሁን ግን ፈጽ​መው በዝ​ተ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእኔ መም​ጣት ባር​ኮ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን ደግሞ ለቤቴ የም​ሠ​ራው መቼ ነው?”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባ​ዛም፤ ሕዝ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ከአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም ከጕ​ል​በ​ትህ ይወ​ጣሉ።


ከአ​ንተ ጋር ያሉ​ትን አራ​ዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር አው​ጣ​ቸው፤ በም​ድ​ርም ላይ ብዙ፤ ተባዙ። ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅ​ንና ልጆ​ቹን ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።


“እነሆ፥ በአ​ንተ ዘንድ የዱር አውሬ አለ፤ እንደ በሬ ሣር ይበ​ላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛ​ውን ለኢ​ዮብ ባረከ፤ መን​ጋ​ዎ​ቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድ​ስት ሺህም ግመ​ሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬ​ዎች፥ አንድ ሺህም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ።


ኃጥ​ኣን በጀ​ር​ባዬ ላይ መቱኝ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም አበ​ዙ​አት።”


የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ወደ ልብ አታመጣም።


ወደ እና​ን​ተም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ አባ​ዛ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች