Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 1:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እግዚእብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፥ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር “ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ የባሕርን ውሃ ይሙላ፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባ​ዙም፤ የባ​ሕ​ር​ንም ውኃ ሙሉ​አት፤ ወፎ​ችም በም​ድር ላይ ይብዙ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እግዚእብሔርም እንድህ ብሎ ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኂ ሙሉአት ውፎችም በምድር ላይ ይብዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 1:22
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተራብተውና ተባዝተው ምድርን ሁሉ እንዲሞሉ ከአንተ ጋር ያሉትን ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ወፎችን፥ እንስሶችንና ሌሎችን በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረቶች ሁሉ ይዘህ ውጣ።”


ባረካቸውም እጅግም በዙ፥ እንስሶቻቸውንም አላሳነሰባቸውም።


አንተን እንደሠራሁ የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፥ እንደ በሬ ሣር ይበላል።


እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፥ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።


ጌታም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፥ ዐሥራ አራት ሺህም በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩት።


እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት።


የጌታ በረከት ሀብታም ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርሷ ጋር አይጨምርም።


ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፥ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።


ስለ ጽኑ ፍቅሩ፥ ለሰው ልጆች ስላደረገው ተአምራት ጌታን ያመስግኑ።


ወደ እናንተም ዘወር ብዬ በበጎ እመለከታችኋለሁ፥ እንድታፈሩም አደርጋችኋለሁ፥ አበዛችሁማለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።


እግዚአብሔርም አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፥ ብዛ፥ ተባዛም፥ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጉልበትህ ይወጣሉ።


ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፥ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ፥ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?”


ላባም፦ “በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚህ ተቀመጥ፥ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና” አለው።


እግዚእብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውን ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።


ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አምስተኛ ቀን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች