Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ንጉ​ሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ሽም ማል​ደው የሚ​በሉ፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ ወዮ​ልሽ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አንቺ፣ ንጉሥሽ ልጅ የሆነ፣ መሳፍንትሽም በጧት ግብዣ የሚያደርጉ ምድር ሆይ፤ ወዮልሽ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሕፃን የሆነ ንጉሥና እየደገሱ ገና በማለዳ የሚሰክሩ መሳፍንት ያሉአት አገር ወዮላት

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 10:16
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም አባቴ ከባድ ቀን​በር ጭኖ​ባ​ች​ኋል፥ እኔ ግን በቀ​ን​በ​ራ​ችሁ ላይ እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ች​ኋል፥ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው።” ይህም ቃል ሮብ​ዓ​ምን ደስ አሰ​ኘው።


ክፉ​ዎች ሰዎ​ችና የሕግ ተላ​ላ​ፊ​ዎች ልጆ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሮብ​ዓም ሕፃን በነ​በ​ረና በልቡ ድፍ​ረት ባል​ነ​በ​ረው ጊዜ፥ ሊቋ​ቋ​መ​ውም ባል​ቻ​ለ​በት ጊዜ፥ በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ላይ በረ​ታ​በት።


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።


ኢዮ​አ​ክ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ ሦስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ነገሠ። 2 ‘ሀ’ የእ​ና​ቱም ስም ከሎ​ቤና የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ አሚ​ጣል ነበ​ረች። 2 ‘ለ’ አባ​ቶቹ እንደ ሠሩት ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሥራን ሠራ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ በኤ​ማት ምድር በዴ​ብ​ላታ ፈር​ዖን ኒካዑ ማርኮ አሰ​ረው።


ኢዮ​አ​ቄ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ዘካራ የም​ት​ባል የኔ​ሬ​ያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበ​ረች፤ አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ። 5 ‘ሀ’ በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ​ዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት። ከእ​ር​ሱም ከዳ። 5 ‘ለ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንና የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንና የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ንን ልጆ​ችና የሰ​ማ​ር​ያን አደጋ ጣዮች ላከ​በት፤ ከዚ​ህም በኋላ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ በነ​ቢ​ያት እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ራቁ። 5 ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለ​ሠ​ራ​ቸው ኀጢ​አ​ቶ​ችና ኢዮ​አ​ቄም ስላ​ፈ​ሰ​ሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ነበር። 5 ‘መ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው አል​ፈ​ለ​ገም ነበር።


ኢኮ​ን​ያ​ንም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የዐ​ሥራ ስም​ንት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ከዐ​ሥር ቀን ነገሠ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።


የሰ​ነፍ ድካሙ ያሠ​ቃ​የ​ዋል፥ ወደ ከተማ መሄ​ድን አያ​ው​ቅ​ምና።


ሕዝቤ ሆይ፥ ገዥ​ዎ​ቻ​ችሁ ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል፤ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ሴቶ​ችም በላ​ያ​ችሁ ይሠ​ለ​ጥ​ኑ​ባ​ች​ኋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​አ​ችሁ ያስ​ቱ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያጠ​ፋሉ።


የዳ​ዊት ቤት ሆይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራ​ችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድና ማንም ሳያ​ጠ​ፋው እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል፥ በማ​ለዳ ፍር​ድን አድ​ርጉ፤ የተ​ነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው እጅ አድኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች