Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 2:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ደግ​ሞም አለ፦ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ የአ​ር​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ተሻ​ገሩ፤ እነሆ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ግዛት፤ ውረ​ሳት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “አሁኑኑ ተነሡና የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ እነሆ፤ የሐሴቦንን ንጉሥ፣ አሞራዊውን ሴዎንንና አገሩን በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ፤ ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ጦርነት ግጠሙት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ደግሞም አለ፦ ‘ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፥ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርሷን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “በሞአብ በኩልም ካለፍን በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለን፦ ‘አሁን ተነሥታችሁ የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ በሐሴቦን ተቀምጦ የሚገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ከነምድሩ ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁ፤ እርሱን ወግታችሁ ምድሩን ውረሱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 2:24
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ እር​ሱም በይ​ሁዳ ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ አዝ​ዞ​ኛል፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ እር​ሱም ይውጣ።”


“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ በይ​ሁ​ዳም ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ እን​ዳ​ስብ አደ​ረ​ገኝ፤


ምድ​ሪ​ቱን፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ​ትን ሰዎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን በታ​ላቅ ኀይ​ሌና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችው ክንዴ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ ለዐ​ይ​ኔም መል​ካም ለሆ​ነው እሰ​ጣ​ታ​ለሁ።


ስለ እኔ ሠር​ተ​ዋ​ልና በጢ​ሮስ ላይ ስለ አገ​ለ​ገ​ለው አገ​ል​ግ​ሎት የግ​ብ​ፅን ምድር ደመ​ወዝ አድ​ርጌ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከዚ​ያም ተጕ​ዘው በዘ​ሬድ ሸለቆ ሰፈሩ።


በአ​ር​ኖን ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔ​ርና በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ካለ​ችው ከተማ ጀም​ረን እስከ ገለ​ዓድ ተራራ ድረስ ማን​ኛ​ዪ​ቱም ከተማ አላ​መ​ለ​ጠ​ች​ንም፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ በዞ​ሩና ካህ​ናቱ ቀንደ መለ​ከ​ቱን በነፉ ጊዜ፤ ኢያሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና ጩኹ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች