ዘዳግም 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ስምህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤ ድንጋጤም ይይዛቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ፣ ማስደንገጣችሁና ማስፈራታችሁ እንዲያድርባቸው ከዚህች ከዛሬዋ ዕለት እጀምራለሁ። ስለ እናንተ ሰምተው ይርበተበታሉ፤ ከእናንተ የተነሣም ይጨነቃሉ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ከሰማይ በታች ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን ማኖር ዛሬ እጀምራለሁ፥ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።’” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦች እናንተን እንዲፈሩ አደርጋለሁ፤ ስለ እናንተ በሰሙ ቊጥር ሁሉም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ።’ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል። ምዕራፉን ተመልከት |