Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 2:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ደግሞም አለ፦ ‘ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፥ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርሷን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “አሁኑኑ ተነሡና የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ እነሆ፤ የሐሴቦንን ንጉሥ፣ አሞራዊውን ሴዎንንና አገሩን በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ፤ ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ጦርነት ግጠሙት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “በሞአብ በኩልም ካለፍን በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለን፦ ‘አሁን ተነሥታችሁ የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ በሐሴቦን ተቀምጦ የሚገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ከነምድሩ ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁ፤ እርሱን ወግታችሁ ምድሩን ውረሱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ደግ​ሞም አለ፦ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ የአ​ር​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ተሻ​ገሩ፤ እነሆ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ግዛት፤ ውረ​ሳት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 2:24
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእኔ ሠርተዋልና ለሠራው ሥራ ካሳ የግብጽን ምድር ሰጥቼዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ምድሪቱን በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ለዓይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።


“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማይ አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ጌታ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም ይውጣ።’ ”


በሰባተኛውም ጊዜ ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ጌታ ከተማይቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።


በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ “የሰማያት አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል፤


ከዚያም ተጉዘው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች