Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እነሆ፥ ሰማይ፥ ሰማየ ሰማ​ያ​ትም፥ ምድ​ርም፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያለው ሁሉ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሰማያት፣ ሰማየ ሰማያት፣ ምድርና በርሷም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርሷም ያለው ሁሉ የጌታ የአምላክህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሰማይና ከሰማይ በላይ ያሉ ሰማያት፥ ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ማናቸውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 10:14
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ራ​ም​ንም ባረ​ከው፤ “አብ​ራም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለፈ​ጠረ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረከ ነው፤


አብ​ራ​ምም የሰ​ዶ​ምን ንጉሥ አለው፥ “ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ወደ ፈጠረ ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጄን ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤


“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ ሰማይ ከሰ​ማ​ያ​ትም በላይ ያለው ሰማይ ይይ​ዝህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ይል​ቁ​ንስ እኔ ለስ​ምህ የሠ​ራ​ሁት ቤት እን​ዴት ያንስ!


“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማ​ያ​ትም ይወ​ስ​ንህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ እን​ግ​ዲ​ያስ እኔ የሠ​ራ​ሁት ይህ ቤት ምን​ድን ነው?


ዕዝ​ራም እን​ዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ ሰማ​ዩ​ንና የሰ​ማ​ያት ሰማ​ይን፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ ምድ​ር​ንና በእ​ር​ስዋ ላይ ያሉ​ትን ሁሉ፥ ባሕ​ሮ​ቹ​ንና በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ሁሉ​ንም ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ የሰ​ማ​ዩም ሠራ​ዊት ለአ​ንተ ይሰ​ግ​ዳሉ።


የከ​ሰል እሳት እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠ​ል​በት ምድጃ ከአ​ፍ​ን​ጫው ጢስ ይወ​ጣል።


ሰማየ ሰማ​ያት፥ ከሰ​ማ​ያት በላይ ያለ ውኃም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።


አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ነፍ​ሴን አነ​ሣ​ለሁ።


ደስ​ታ​ንና ማዳ​ን​ህን ስጠኝ፥ በጽኑ መን​ፈ​ስም አጽ​ናኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሆ​ችን ሰም​ቶ​እ​ቸ​ዋ​ልና፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም አል​ና​ቃ​ቸ​ው​ምና።


አሁ​ንም ቃሌን በእ​ው​ነት ብት​ሰሙ፥ ኪዳ​ኔ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ረጠ ርስት ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።


ሙሴም፥ “ለፈ​ር​ዖን ከከ​ተማ በወ​ጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐ​ድ​ጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረ​ዶ​ውም፥ ዝና​ቡም ደግሞ አይ​ወ​ር​ድም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ የም​ት​ሠ​ሩ​ልኝ ቤት ምን ዓይ​ነት ነው? የማ​ር​ፍ​በ​ትስ ስፍራ ምን​ድን ነው?


ዓለ​ሙ​ንና በእ​ር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ የፈ​ጠረ አም​ላክ እርሱ የሰ​ማ​ይና የም​ድር ጌታ ነውና እጅ በሠ​ራው መቅ​ደስ አይ​ኖ​ርም።


“ምድር በመ​ላዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናትና።”


እን​ግ​ዲህ “ይህ ለጣ​ዖት የተ​ሠዋ ነው” ያላ​ችሁ ቢኖር ግን፥ ስለ ነገ​ራ​ች​ሁና ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም የሚ​ጠ​ራ​ጠር ስለ​ሆነ አት​ብሉ።


በክ​ር​ስ​ቶስ ያመነ አንድ ሰው አው​ቃ​ለሁ፤ ዘመኑ ከዐ​ሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥ​ጋው ይሁን በነ​ፍሱ እንጃ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስ​ተ​ኛው ሰማይ ድረስ ነጥ​ቀው ወሰ​ዱት።


መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ ዛሬ ለአ​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት ትጠ​ብቅ ዘንድ ነው እንጂ፤


እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች