Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ተነ​ሥ​ተህ በሕ​ዝቡ ፊት ተጓዝ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ልሰ​ጣ​ቸው ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይግቡ፤ ይው​ረ​ሱ​አ​ትም’ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህም እግዚአብሔር፣ “ሂድ፤ ለአባቶቻቸው ለመስጠት ወደ ማልሁላቸው ምድር ገብተው እንዲወርሱ ሕዝቡን ምራ” አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ‘ተነሥ፥ ለአባቶቻቸውም ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር እንዲገቡ እንዲወርሱአትም፥ ሕዝቡን ምራ።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህም በኋላ ‘እንግዲህ ሂድ፤ ለቀድሞ አባቶቻቸው በሰጠሁት የተስፋ ቃል መሠረት ምድሪቱን እንዲወርሱ ሕዝቡን ምራ’ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔርም፦ ተነሥተህ በሕዝቡ ፊት ተጓዝ፤ ለአባቶቻቸውም ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር ይግቡ ይውረሱአትም አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 10:11
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም ሂድ፤ ይህ​ንም ሕዝብ ወደ ነገ​ር​ሁህ ቦታ ምራ፤ እነሆ፥ መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ቀን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ሂድ፤ አንተ ከግ​ብፅ ከአ​ወ​ጣ​ኸው ሕዝ​ብህ ጋር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ወደ ማል​ሁ​ባት ምድር ውጣ።


እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ግቡ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ውረሱ።


“እኔም እንደ ፊተ​ኛው ጊዜ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተ​ራ​ራው ላይ ቆምሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚህ ጊዜ ደግሞ ሰማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ደም።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አሁ​ንስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈራ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ታመ​ል​ከው ዘንድ ነው እንጂ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች