Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 16:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ንጉሡ አካ​ዝም የመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ችን ክፈፍ ቈረጠ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰኖች ወሰደ፤ ኵሬ​ው​ንም ከበ​ታቹ ከነ​በ​ሩት ከናሱ በሬ​ዎች አወ​ረ​ደው፤ በጠ​ፍ​ጣ​ፋ​ውም ድን​ጋይ ላይ አኖ​ረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ንጉሡ አካዝም የጐንና የጐን ሳንቃዎቹን ነቅሎ ወሰደ፤ በተንቀሳቃሹ መቆሚያ ላይ ያሉትን የመታጠቢያ ሳሕኖች አስወገደ። የውሃ ማጠራቀሚያውን ክብ ገንዳ ከታች ተሸክመው ከያዙት ከዐሥራ ሁለቱ የናስ ቅርጽ ኰርማዎች ላይ አውርዶ በጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ አስቀመጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ንጉሥ አካዝ በቤተ መቅደስ ውስጥ መገልገያ የነበሩትን ከነሐስ የተሠሩ መንኰራኲሮች ቆርጦ ልሙጥ የሆነውን ነገር ከጐናቸው ወሰደ። በእነርሱ ላይ የነበሩትንም የመታጠቢያ ሳሕኖች ወሰደ፤ ከነሐስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ከታች በኩል ተሸክመውት ከነበሩት ከነሐስ ከተሠሩት ከዐሥራ ሁለት የበሬ ቅርጾች ጀርባ ላይ አንሥቶ፥ ከድንጋይ በተሠራ መሠረት ላይ አኖረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ንጉሥ አካዝ በቤተ መቅደስ ውስጥ መገልገያ የነበሩትን ከነሐስ የተሠሩ መንኰራኲሮች ቈርጦ ልሙጥ የሆነውን ነገር ከጐናቸው ወሰደ። በእነርሱ ላይ የነበሩትንም የመታጠቢያ ሳሕኖች ወሰደ፤ ከነሐስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ከታች በኩል ተሸክመውት ከነበሩት ከነሐስ ከተሠሩት ከዐሥራ ሁለት የበሬ ቅርጾች ጀርባ ላይ አንሥቶ፥ ከድንጋይ በተሠራ መሠረት ላይ አኖረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ንጉሡም አካዝ የመቀመጫዎችን ክፈፍ ቈረጠ፤ ከእነርሱም የመታጠቢያውን ሰኖች ወሰደ፤ ኵሬውንም ከበታቹ ከነበሩት ከናሱ በሬዎች አወረደው፤ በጠፍጣፋውም ድንጋይ ላይ አኖረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 16:17
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ካህኑ ኦር​ያም ንጉሡ አካዝ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የዙ​ፋ​ኑን መሠ​ረት ሠራ፤ ስለ አሦ​ርም ንጉሥ በውጭ ያለ​ውን የን​ጉ​ሡን መግ​ቢያ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አዞ​ረው።


አካ​ዝም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ​ዎች ሁሉ ወስዶ ሰባ​በ​ራ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ደጆች ዘጋ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ማዕ​ዘን ሁሉ ለራሱ መሠ​ዊያ ሠራ።


ንጉ​ሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመ​ተ​ላ​ለፉ ያረ​ከ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል፤ ቀድ​ሰ​ና​ልም፤ እነ​ሆም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ሆነ​ዋል” አሉት።


ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ፥ ከመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም በታች የነ​በ​ሩ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን የናስ በሬ​ዎች ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚህ የናስ ዕቃ​ዎች ሁሉ ሚዛን አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች