Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የዙ​ፋ​ኑን መሠ​ረት ሠራ፤ ስለ አሦ​ርም ንጉሥ በውጭ ያለ​ውን የን​ጉ​ሡን መግ​ቢያ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አዞ​ረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የአሦርንም ንጉሥ ለማስደሰት ሲል፣ በዕለተ ሰንበት ንጉሣዊ ዙፋን እንዲዘረጋበት በቤተ መቅደሱ ውስጥ የተሠራውን ከፍ ያለ ስፍራና ነገሥታቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚገቡበትን በውጭ ያለውን መግቢያ አነሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አካዝ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለማስደሰት ሲል ንጉሣዊ ዙፋን የሚዘረጋበትን ሉዓላዊ ስፍራ አስወገደ፤ ከዚያ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ወደ ቤተ መቅደስ ይገባበት የነበረውንም ልዩ በር ዘጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አካዝ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለማስደሰት ሲል ንጉሣዊ ዙፋን የሚዘረጋበትን ሉዓላዊ ስፍራ አስወገደ፤ ከዚያ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ወደ ቤተ መቅደስ ይገባበት የነበረውንም ልዩ በር ዘጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በእግዚአብሔርም ቤት የዙፋኑን መሠረት ሠራ፤ ስለ አሦርም ንጉሥ በውጭ ያለውን የንጉሡን መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቤት አዞረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 16:18
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አለ​ቃው በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መን​ገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠ​ገብ ይቁም፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ር​ሱን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርቡ፥ እር​ሱም በበሩ መድ​ረክ ላይ ይስ​ገድ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይ​ዘጋ።


እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በሰ​ን​በት ቀን ከም​ት​ገ​ቡት ከእ​ና​ንተ ከሦ​ስት አንዱ እጅ በበር ተቀ​ም​ጣ​ችሁ የን​ጉ​ሡን ቤት ዘብ ጠብቁ፤


የሰ​ሎ​ሞ​ን​ንም የማ​ዕ​ዱን መብል፥ የብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም አቀ​ማ​መጥ፥ የሎ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ሥር​ዐት፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ባየች ጊዜ ተደ​ነ​ቀች።


ንጉሡ አካ​ዝም የመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ችን ክፈፍ ቈረጠ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰኖች ወሰደ፤ ኵሬ​ው​ንም ከበ​ታቹ ከነ​በ​ሩት ከናሱ በሬ​ዎች አወ​ረ​ደው፤ በጠ​ፍ​ጣ​ፋ​ውም ድን​ጋይ ላይ አኖ​ረው።


የቀ​ረ​ውም አካዝ ያደ​ረ​ገው ነገር እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


እስ​ከ​ዛ​ሬም ድረስ በን​ጉሥ በር በም​ሥ​ራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረ​ኞች ነበሩ።


አለ​ቃው ግን እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ታል፤ በበሩ ይገ​ባል፤ በዚ​ያም መን​ገድ ይወ​ጣል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች