Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እና​ንተ እን​ደ​ም​ት​ተጉ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ስለ​ዚ​ህም “የአ​ካ​ይያ ሰዎች እኮ ከአ​ምና ጀምሮ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋል” ብዬ በመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ዘንድ አመ​ሰ​ገ​ን​ኋ​ችሁ፤ እነ​ሆም የእ​ና​ንተ መፎ​ካ​ከር ብዙ​ዎ​ችን ሰዎች አት​ግ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ምክንያቱም ሌሎችን ለመርዳት ያላችሁን በጎ ፈቃድ ዐውቃለሁ፤ ካለፈው ዓመት ጀምሮ እናንተ በአካይያ የምትኖሩ ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ እንደ ሆናችሁ ለመቄዶንያ ሰዎች አፌን ሞልቼ ተናግሬአለሁ፤ ቅን ፍላጎታችሁም ብዙዎችን ለበጎ ሥራ አነሣሥቷል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በጎ ፈቃዳችሁን ስለማውቅ፤ በእናንተ ላይ የምመካበትን ምክንያት ለመቄዶንያ ሰዎች፥ “አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቶአል፤” ብዬ ተናግሬለሁ፤ ቅንዐታችሁም ብዙዎችን አነሣሥቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የዐካይያ ሰዎች ከዐለፈው ዓመት ጀምረው ለመርዳት ዝግጁዎች ናቸው” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ ስለ እናንተ የምመካው ትጋታችሁን ስለማውቅ ነው፤ የእናንተም ትጋት ሌሎችን አነሣሥቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በጎ ፈቃዳችሁን አውቄአለሁና፤ ስለዚህም፦ አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቶአል ብዬ ለመቄዶንያ ሰዎች በእናንተ እመካለሁ፥ ቅንዓታችሁም የሚበዙቱን አነሣሥቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 9:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጋል​ዮ​ስም የአ​ካ​ይያ አገረ ገዢ በሆነ ጊዜ አይ​ሁድ ተባ​ብ​ረው በጳ​ው​ሎስ ላይ ተነሡ፤ ወደ ሸን​ጎም አመ​ጡት።


ከብዙ ዓመ​ታ​ትም በኋላ ለወ​ገ​ኖች ምጽ​ዋ​ት​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ላደ​ርግ መጣሁ።


መቄ​ዶ​ን​ያና አካ​ይያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅዱ​ሳን መካ​ከል ላሉ ድሆች አስ​ተ​ዋ​ጽ​ፅኦ ለማ​ድ​ረግ ተባ​ብ​ረ​ዋ​ልና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስና የፈ​ር​ዶ​ና​ጥስ፥ የአ​ካ​ይ​ቆ​ስም ቤተ​ሰ​ቦች፥ የአ​ካ​ይያ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ለማ​ገ​ል​ገል ራሳ​ቸ​ውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ከሆነ ጳው​ሎ​ስና ከወ​ን​ድ​ማ​ችን ጢሞ​ቴ​ዎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሀገር ላለ​ችው የእ​ግ​ዚ​አ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንና በአ​ካ​ይያ ሀገር ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፥


ስለ እና​ንተ ለእ​ርሱ በተ​መ​ካ​ሁ​በት ሁሉ አላ​ሳ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእ​ና​ንተ በእ​ው​ነት እንደ ተና​ገ​ርን፥ እን​ደ​ዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትም​ክ​ህ​ታ​ችን እው​ነት ሆነ።


በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ዲሁ ብዙ መወ​ደድ አለኝ፤ ስለ እና​ን​ተም የም​መ​ካ​በት ብዙ ነው፤ መጽ​ና​ና​ት​ንም አገ​ኘሁ፤ ከመ​ከ​ራ​ዬም ሁሉ ይልቅ ደስ​ታዬ በዛ​ልኝ።


በዚ​ህም የሚ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁን እመ​ክ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይህን ከማ​ድ​ረ​ጋ​ችሁ በፊት ፈቅ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ከአ​ምና ጀም​ሮም ይህን ጀም​ራ​ች​ኋል።


አሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ፈጽ​ሙም፤ መፍ​ቀድ ከመ​ሻት ነውና፤ ማድ​ረ​ግም ከማ​ግ​ኘት ነውና።


ይህም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብ​ርና የእ​ኛን በጎ ፈቃድ ለማ​ሳ​የት በም​ና​ገ​ለ​ግ​ል​ባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ተሾመ።


አሁ​ንም መዋ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ንና እኛም በእ​ና​ንተ የም​ን​መ​ካ​በ​ትን ሥራ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ፊት በግ​ልጥ አሳ​ዩ​አ​ቸው።


በግድ የም​ላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ለዚህ ሥራ የሚ​ተ​ጉ​ለት አሉና የፍ​ቅ​ራ​ች​ሁን እው​ነ​ተ​ኛ​ነት አሁን መር​ምሬ ተረ​ዳሁ።


ስለዚህም በመቄዶንያና በአካይያ ላሉት ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው።


በፍ​ቅ​ርና በበጎ ምግ​ባ​ርም ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችን ጋር እን​ፎ​ካ​ከር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች