Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 5:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃሌን አድምጥ፤ መቃተቴንም ቸል አትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሆይ! ቃሌን አድምጥ፤ መቃተቴንም ስማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ ቃሌን አድ​ምጥ፥ ጩኸ​ቴ​ንም አስ​ተ​ውል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 5:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ ጩኸቴንም ስማ፤ ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ ጸሎቴን አድምጥ።


ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤ የአፌንም ቃል አድምጥ።


አምላክ ሆይ፤ የብሶት ቃሌን ስማ፤ ሕይወቴንም ከሚያስፈራ የጠላት ዛቻ ከልላት።


ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፤ በብርሃንህ ተገለጥ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል፤ ስማኝም፤ እኔ ችግረኛ ድኻ ነኝና።


እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል።


ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።”


እርሷም በልቧ ትጸልይ ስለ ነበር፤ ከንፈሯ ይንቀሳቀስ እንጂ ድምፅዋ አይሰማም ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከረች አድርጎ ቈጠራት።


ይህን ያህል ጊዜ የጸለይሁት ከባድ ከሆነው ጭንቀቴና ሐዘኔ የተነሣ ስለ ሆነ፣ አገልጋይህን እንደ ምናምንቴ ሴት አትቍጠረኝ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች