Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 9:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነርሱም ኢያሱን፣ “እኛ ባሪያዎችህ ነን” አሉት። ኢያሱ ግን፣ “እናንተ እነማን ናችሁ? የመጣችሁትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ነን።” ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የገባዖንም ሰዎች ኢያሱን “እኛ አገልጋዮችህ ነን” አሉት። ኢያሱም “እናንተ እነማን ናችሁ? የመጣችሁትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ኢያ​ሱ​ንም፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገ​ርም ነን” አሉት። ኢያ​ሱም፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ? ከወ​ዴ​ትስ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ኢያሱንም፦ እኛ ባሪያዎችህ ነን አሉት። ኢያሱም፦ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ? አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 9:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፣ የከተማዪቱ ገዥ፣ ሽማግሌዎችና የልጆቹ ሞግዚቶች፣ “እኛ የአንተው አገልጋዮች ነን፤ ትእዛዝህን ሁሉ እንፈጽማለን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አንተው አድርግ” በማለት ይህን መልእክት ለኢዩ ላኩ።


ከተቀበሉህና ደጃቸውን ከከፈቱልህ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ ገባርህ ይሁን፤ ያገልግልህም።


የገባዖንም ሰዎች በጌልገላ ወደ ሰፈረው ወደ ኢያሱ፣ “በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ኀይላቸውን አስተባብረው ተሰልፈውብናል፤ እኛን ባሮችህን አትተወን፤ ርዳን፤ ፈጥነህ በመድረስም አድነን” ሲሉ ላኩበት።


ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፣ ‘ለመንገዳችሁ የሚሆን ስንቅ ያዙ፤ ሄዳችሁም ተገናኟቸው፤ “እኛ ባሮቻችሁ እንሆናለን፤ ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን ግቡ” በሏቸው’ አሉን።


ስለዚህ አሁን የተረገማችሁ ናችሁ፤ ጥቂቶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ምን ጊዜም ዕንጨት ቈራጭ፣ ውሃ ቀጂ ባሮች ትሆናላችሁ።”


እነሆ፤ አሁን በእጅህ ውስጥ ነን፤ በጎና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።”


በዚያችም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር ለሆነው መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ ዕንጨት ቈራጮችና ውሃ ቀጂዎች አደረጋቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች