Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ኢያ​ሱ​ንም፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገ​ርም ነን” አሉት። ኢያ​ሱም፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ? ከወ​ዴ​ትስ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነርሱም ኢያሱን፣ “እኛ ባሪያዎችህ ነን” አሉት። ኢያሱ ግን፣ “እናንተ እነማን ናችሁ? የመጣችሁትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ነን።” ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የገባዖንም ሰዎች ኢያሱን “እኛ አገልጋዮችህ ነን” አሉት። ኢያሱም “እናንተ እነማን ናችሁ? የመጣችሁትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ኢያሱንም፦ እኛ ባሪያዎችህ ነን አሉት። ኢያሱም፦ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ? አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 9:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአ​ክ​አ​ብም የቤቱ አለ​ቆች፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹና ልጆ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ን​ንም ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ የም​ና​ነ​ግ​ሠው ሰው የለም፤ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አድ​ርግ” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።


የሰ​ላም ቃልም ቢመ​ል​ሱ​ልህ ደጅም ቢከ​ፍ​ቱ​ልህ፥ በከ​ተ​ማው ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገ​ብ​ሩ​ልህ፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ይሁ​ኑህ።


የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ ጌል​ገላ ልከው፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ለመ​ር​ዳት እጅ​ህን አት​መ​ልስ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር የሚ​ኖሩ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በ​ው​ብ​ና​ልና ፈጥ​ነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድ​ነ​ንም፤ ርዳ​ንም፤” አሉት።


ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ንና የሀ​ገ​ራ​ችን ሰዎች ሁሉ፦ ለመ​ን​ገድ ስንቅ ያዙ፤ ልት​ገ​ና​ኙ​አ​ቸ​ውም ሂዱ፦ እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ነን፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ በሉ​አ​ቸው አሉን።


አሁ​ንም የተ​ረ​ገ​ማ​ችሁ ሁኑ፤ ለእ​ኔም፥ ለአ​ም​ላ​ኬም እን​ጨት ቈራጭ፥ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእ​ና​ንተ አይ​ጠ​ፋም” አላ​ቸው።


አሁ​ንም እነሆ፥ በእ​ጃ​ችሁ ውስጥ ነን፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁና ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ችሁ አድ​ር​ጉ​ብን” አሉት፤


በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች