Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 31:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምርኳቸውን በመለስሁላቸው ጊዜ፣ እነርሱ በይሁዳ ምድርና በከተሞቿ፣ ‘አንተ የጽድቅ ማደሪያ ቅዱስ ተራራ ሆይ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ!’ የሚል አነጋገር እንደ ገና ይጠቀማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የእስራኤል አምላክ የሠርዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ አገር በከተሞችዋ፦ ‘የጽድቅ ማደሪያ ሆይ! የቅድስና ተራራ ሆይ! ጌታ ይባርክህ’ የሚልን ቃል እንደገና ይናገራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቡን ወደ አገራቸው በመለስኩ ጊዜ በይሁዳና በከተሞቹ እንደገና ‘አንቺ የእውነት ማደሪያ የሆንሽ ቅድስት ተራራ እግዚአብሔር ይባርክሽ’ ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን በመ​ለ​ስሁ ጊዜ በይ​ሁዳ ሀገር በከ​ተ​ሞ​ችዋ፦ የጽ​ድቅ ማደ​ሪያ ሆይ! የቅ​ድ​ስና ተራራ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ የሚል ነገ​ርን እንደ ገና ይና​ገ​ራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የእስራኤል አምላክ የሠርዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ አገር በከተሞችዋ፦ የጽድቅ ማደሪያ ሆይ፥ የቅድስና ተራራ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ የሚልን ነገር እንደ ገና ይናገራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 31:23
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፤


መንገድ ዐላፊዎችም፣ “የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ።


ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር፣ ከጽዮን ይባርክህ።


ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤ እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።


ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደ ሆነች ተመልከቱ፤ ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፣ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤ አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነች፤


ፈራጆችሽን እንደ ጥንቱ፣ አማካሪዎችሽንም እንደ ቀድሞው እመልሳለሁ፤ ከዚያም የጽድቅ መዲና፣ የታመነች ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።”


በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ጕዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤ ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።


በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤ በለሙም መሬት ጽድቅ ይኖራል፤


እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጧልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በጽድቅና በፍትሕ ይሞላታል።


ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ፤ ለክብሬ መግለጫ ይሆኑ ዘንድ፣ የእጆቼ ሥራ፣ እኔ የተከልኋቸው ቍጥቋጦች ናቸው።


እኔም እገኝላችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከምርኮም እመልሳችኋለሁ፤ እናንተንም ከበተንሁበት አገርና ስፍራ ሁሉ እመልሳችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምርኮ ምክንያት ወዳስለቀቅኋችሁም ምድር እመልሳችኋለሁ።”


“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማዪቱ በፍርስራሿ ጕብታ ላይ ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በቀድሞ ቦታው ይቆማል።


ምርኳቸውን ስለምመልስላቸው በብንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች፣ በይሁዳ ከተሞችና በተራራማው አገር ከተሞች፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች፣ መሬት በጥሬ ብር ይገዛል፤ ውሉም ተፈርሞ፤ በምስክሮች ፊት ይታሸጋል፤’ ይላል እግዚአብሔር።”


ያገኛቸው ሁሉ ይውጣቸዋል፤ ጠላቶቻቸውም፣ ‘እኛ በደለኞች አይደለንም፤ እነርሱ የአባቶቻቸውን ተስፋ እግዚአብሔርን፣ እውነተኛ ማደሪያቸው የሆነውን እግዚአብሔርን በድለዋል’ አሉ።


ነገር ግን በጽዮን ተራራ ነጻ መውጣት ይሆናል፤ የያዕቆብ ቤትም እርሷ የተቀደሰች ትሆናለች፤ ርስታቸውን ይወርሳሉ።


በመጨረሻው ዘመን፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ፣ ከተራሮችም ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤ በኢየሩሳሌም እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ተራራም ቅዱስ ተራራ ይባላል።”


በዚሁ ጊዜ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፤ ዐጫጆቹንም፣ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን!” ብሎ ሰላምታ ሰጣቸው። እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ይባርክህ!” ብለው መለሱለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች