Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 10:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የሕዝቦች ሁሉ ንጉሥ ሆይ፤ አንተን የማይፈራ ማነው? ክብር ይገባሃልና። ከምድር ጠቢባን ሁሉ፣ ከመንግሥቶቻቸውም ሁሉ መካከል፣ እንደ አንተ ያለ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ ሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የመንግሥታት ሁሉ ንጉሥ ስለ ሆንክ አንተን የማይፈራ ማን ነው? በአሕዛብ ጠቢባንም ሆነ በንጉሦቻቸው መካከል አንተን የሚመስል ስለሌለ ክብር ይገባሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 10:7
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይልቅስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ከጠላቶቻችሁ ሁሉ እጅ የሚታደጋችሁ እርሱ ነውና።”


እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴውም ብዙ ነው፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል።


ሕግንና ፍትሕን በተመለከተ የሊቃውንቱን ምክር መጠየቅ በንጉሥ ዘንድ የተለመደ ነበርና፣ ስለ ዘመናት ሁኔታ ዕውቀት ካላቸው ጠቢባን ጋራ ተነጋገረበት፤


ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ ለጥበቡም ወሰን የለውም።


መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤ ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው።


ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤ መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን።


ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል።


መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤ በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል?


ጌታ ሆይ፤ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤ ከአንተም ሥራ ጋራ የሚወዳደር ሥራ የለም።


ጌታ ሆይ፤ አንተ የሠራሃቸው ሕዝቦች ሁሉ፣ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ፤ ለስምህም ክብር ይሰጣሉ፤


በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋራ ማን ሊስተካከል ይችላል? ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?


ፈርዖንም፣ “ነገ ይሁን” አለው። ሙሴም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ ታውቅ ዘንድ አንተ እንዳልኸው ይሆናል።


አለዚያ በአንተ በሹማምትህና በሕዝብህ ላይ የመቅሠፍቴን መዓት ሁሉ አሁን አወርድብሃለሁ፤ ይኸውም በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ ማንም እንደሌለ ታውቅ ዘንድ ነው።


እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።


እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ፤ የስምህም ሥልጣን ታላቅ ነው።


ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን? ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣ አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።


ዳንኤልም እንዲህ አለ፤ “አንድም ጠቢብ፣ አስማተኛ፣ ጠንቋይም ሆነ ቃላተኛ ንጉሡ የጠየቀውን ምስጢር መግለጥ የሚችል የለም፤


ነገር ግን ምስጢርን የሚገልጥ አምላክ በሰማይ አለ፤ እርሱም በሚመጡት ዘመናት የሚሆነውን ነገር ለንጉሥ ናቡከደነፆር ገልጧል፤ በዐልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ በአእምሮህ የነበረው ሕልምና ራእይ ይህ ነው፤


እግዚአብሔር ሆይ፤ ዝናህን ሰምቻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህም አስፈራኝ፤ በእኛ ዘመን አድሳቸው፤ በእኛም ጊዜ እንዲታወቁ አድርግ፤ በመዓት ጊዜ ምሕረትን ዐስብ።


“በዚያ ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ። በመካከልሽ እኖራለሁ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ አንቺ እንደ ላከኝም ታውቃላችሁ።


“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን መፍራት የሚገባችሁን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን እርሱን ፍሩት፤ አዎን፣ እርሱን ፍሩት እላችኋለሁ።


ለእኛ ግን ሁሉም ነገር ከርሱ የሆነ፣ እኛም ለርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፤ ደግሞም ሁሉም ነገር በርሱ አማካይነት የሆነ፣ እኛም በርሱ አማካይነት የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።


ይህን ያደረገውም፣ የእግዚአብሔር ክንድ ብርቱ መሆኑን የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንዲያውቁና እናንተም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለዘላለም እንድትፈሩ ነው።”


ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፤ “የዓለም መንግሥት፣ የጌታችንና የርሱ ክርስቶስ መንግሥት ሆነች፤ እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”


ጌታ ሆይ፤ አንተን የማይፈራ፣ ስምህን የማያከብርስ ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና። የጽድቅ ሥራህ ስለ ተገለጠ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች