Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 19:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 አሳፋሪና አስነዋሪ የሆነ ልጅ አባቱን ያጒላላል፤ እናቱንም ከቤት ያባርራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አባቱን የሚዘርፍ፣ እናቱንም የሚያሳድድ፣ ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 አባቱን የሚያስከፋ እናቱንም የሚያሳድድ የሚያሳፍርና ጐስቋላ ልጅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አባቱን የሚያዋርድ እናቱንም የሚያሳድድ፥ አሳፋሪና ጐስቋላ ልጅ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 19:26
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነዚህ የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።


ብልኅ ሰው መከሩን በወቅቱ ይሰበስባል፤ በመከር ወራት የሚተኛ ግን ውርደት ይደርስበታል።


የጌታው ልጅ ወራዳ ከሆነ ብልኅ አገልጋይ በጌታው ልጅ ላይ የበላይነት ይኖረዋል፤ ከወንድማማቾቹም ጋር ርስት ተካፋይ ይሆናል።


ሰነፍ ልጅ አባቱን በሐዘን ላይ ይጥላል፤ በእናቱም ላይ መራራ ጸጸት ያመጣል።


ልጄ ሆይ! ምክሬን ባትሰማ የምታውቀውን ትምህርት እንኳ በቶሎ ረስተህ ትሳሳታለህ።


ሁልጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የተባረከ ነው፤ እምቢተኛ የሚሆን ሰው ግን ችግር ላይ ይወድቃል።


ከአባቱና ከእናቱ ሰርቆ “ኃጢአት አላደረግሁም” የሚል ሰው ከማንኛውም አጥፊ ሰው የተሻለ አይደለም።


ሕግን የሚያከብር ልጅ ጥበበኛ ነው፤ ከማይረቡ ወስላቶች ጋር ወዳጅ የሚሆን ልጅ ግን አባቱን ያሳፍራል።


አባቶቻቸውን የሚሰድቡ፥ እናቶቻቸውንም የማያመሰግኑ ሰዎች አሉ።


በአባቱ የሚያፌዝና እናቱ በምታረጅበት ጊዜ የሚንቃት ሰው የሸለቆ ቊራዎች ዐይኖቹን ጐጥጒጠው ያወጡታል፤ ጆፌ አሞራዎችም ይበሉታል።


ይህ ልጅህ ግን ሀብትህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በተመለሰ ጊዜ የሰባውን ወይፈን ዐረድክለት።’


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች