Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 19:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ፌዘኛ ብትቀጣው አላዋቂው ብልኅ ይሆናል፤ አስተዋይ ሰው ብትገሥጸው የበለጠ ዕውቀትን ይጨምራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ፌዘኛን ግረፈው፤ አላዋቂውም ማስተዋልን ይማራል፤ አስተዋይን ዝለፈው፤ ዕውቀትን ይገበያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ፌዘኛ ብትገርፈው አላዋቂ ብልሃተኛ ይሆናል፥ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው እውቀትን ያገኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ፌዘኛን ብትገርፈው አላዋቂው ብልሃተኛ ይሆናል፤ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው ግን ዕውቀትን ያገኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 19:25
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።


እነዚህ ምሳሌዎች ጠቢባን ዕውቀታቸውን እንዲያዳብሩ፥ አስተዋዮችም ተጨማሪ መመሪያ የሚሆናቸውን ምክር እንዲያገኙ ያደርጋሉ።


ሞኝ የአባቱን ምክር ይንቃል፤ ተግሣጽን የሚቀበል ግን አስተዋይ ነው።


ሞኝ መቶ ጊዜ ተገርፎ ከሚማረው ይልቅ አስተዋይ ሰው ከአንድ ጊዜ በማይበልጥ ተግሣጽ የሚማረው ይበልጣል።


ፌዘኛ በሚቀጣበት ጊዜ አላዋቂ ሰው ጥበብን ያገኛል፤ ለብልኅም ሰው ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ የበለጠ ዐዋቂ ይሆናል።


ትዕቢተኛን ሰው ብታርመው ስድብን ታተርፋለህ፤ ክፉውን ሰው ብትገሥጸው ጒዳት ይደርስብሃል።


ከዚህም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የሆነውን ነገር ሰምተው ይፈራሉ፤ ስለዚህም ያንን ዐይነት ክፉ ነገር እንደገና የሚያደርግ አይኖርም።


የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ወግረው ይግደሉት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ታስወግዳላችሁ፤ በእስራኤልም የሚኖር ሁሉ ይህን ሁኔታ ሰምቶ ይፈራል።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች