Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 3:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ለያንዳንዱ መዋጃ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት አምስት ሰቅል የሚመዝን ብር ትወስዳለህ፤ አንዱ ሰቅል ኻያ ጌራ ነው (ጌራ 0.6 ግራም ነው)።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ለእያንዳንዱ በኵር ክብደቱ ባለሃያ አቦሊ በሆነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ልክ ዐምስት ዐምስት ሰቅል ተቀበል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ለእያንዳንዱ አምስት ሰቅል ውሰድ፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ፤ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 በየ​ራሱ አም​ስት ዲድ​ር​ክም ውሰድ፤ እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ብዛት ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ፤ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 3:47
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሕዝብ ቈጠራ ውስጥ የሚገባ እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እያንዳንዱ ሰው ይህን ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ያቅርብ፤


ለተቀደሰው ድንኳን መሥሪያ ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሔር ተለይቶ የተሰጠ ወርቅ በሙሉ በይፋ በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ሺህ ኪሎ ግራም ይመዝን ነበር


“ሚዛናችሁም፥ ኻያ ጌራህ አንድ ሰቅል፥ ሥልሳ ሰቅል አንድ ምናን ይሁን፤


“ዋጋቸው ሁሉ የሚተመኑት በቤተ መቅደሱ የሰቅል ሚዛን መሠረት ሲሆን አንዱ ሰቅል ሃያ ጌራ (0.6 ግራም) ነው።


በቤተ መቅደሱስ በታወቀው ሚዛን ልክ ዕድሜው ከኻያ እስከ ሥልሳ ለሆነ ወንድ 600 ግራም የሚመዝን ጥሬ ብር ይሁን፤


ዕድሜው ከአንድ ወር እስከ አምስት ዓመት ለሆነ ወንድ አምስት ጥሬ ብር፥ በዚሁ ዕድሜ ክልል ውስጥ ለምትገኝ ሴት ሦስት ጥሬ ብር ይሁን፤


አንድ ወር የሞላቸው ሕፃናት በይፋ በተመደበው ዋጋ መሠረት አምስት ሰቅል ጥሬ ብር የቤዛ ዋጋ ተከፍሎላቸው ሊዋጁ ይችላሉ።


ይህንንም የመዋጃ ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ።”


ከእስራኤላውያን በኲሮች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት ገንዘቡን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሥልሳ አምስት ሰቅል ብር ወሰደ።


ያቀረባቸውም መባዎች እነዚህ ናቸው፦ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን አንድ ከብር የተሠራ ዝርግ ሳሕን፥ ከሰባ ሰቅል ብር የተሠራ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፥ ሁለቱም ለእህል ቊርባን በሚሆን ከዘይት ጋር በተቀላቀለ ደቃቅ ዱቄት የተሞሉ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች