Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 3:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 በየ​ራሱ አም​ስት ዲድ​ር​ክም ውሰድ፤ እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ብዛት ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ለእያንዳንዱ በኵር ክብደቱ ባለሃያ አቦሊ በሆነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ልክ ዐምስት ዐምስት ሰቅል ተቀበል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ለእያንዳንዱ አምስት ሰቅል ውሰድ፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ፤ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ለያንዳንዱ መዋጃ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት አምስት ሰቅል የሚመዝን ብር ትወስዳለህ፤ አንዱ ሰቅል ኻያ ጌራ ነው (ጌራ 0.6 ግራም ነው)።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ፤ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 3:47
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአ​ንድ ወርም እስከ አም​ስት ዓመት ድረስ ለወ​ንድ ግምቱ አም​ስት የብር ዲድ​ር​ክም፥ ለሴ​ትም ግምቷ ሦስት የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን።


ይቈ​ጠሩ ዘንድ የሚ​ያ​ል​ፉት ሁሉ የሚ​ሰ​ጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ይሰ​ጣል። ሰቅ​ሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰ​ቅ​ሉም ግማሽ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ነው።


አንድ ወር የሆ​ነው ልጅ ዋጋው በቤተ መቅ​ደስ ሚዛን አም​ስት ሰቅል ነው። ይኸ​ውም ሃያ አቦሊ ነው።


ግም​ቱም ሁሉ እንደ መቅ​ደሱ ሚዛን ይሆ​ናል፤ አንዱ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ይሆ​ናል።


ሰቅ​ሉም ሃያ አቦሊ ይሁን፤ ሃያ ሰቅል፥ ሃያ አም​ስት ሰቅል፥ ዐሥራ አም​ስት ሰቅል፥ ምናን ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ሮች ገን​ዘ​ቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ሚዛን ወሰደ።


የተ​ሰ​ጠው ወርቅ ሁሉ፥ ለድ​ን​ኳኑ ሥራ ሁሉ የተ​ደ​ረ​ገው ወርቅ፥ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ሃያ ዘጠኝ መክ​ሊት ሰባት መቶ ሠሳሳ ሰቅል ነበረ።


ለወ​ንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስድሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅ​ደሱ ሚዛን ግምቱ አምሳ የብር ዲድ​ር​ክም ይሁን።


ስለ ተረ​ፉ​ትም የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች