Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 3:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 በኲር ሆነው የተወለዱት የእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ብዛት፥ ከሌዋውያን ብዛት በሁለት መቶ ሰባ ሦስት ስለሚበልጥ እነዚህን ትርፍ የሆኑትን ወንዶች ልጆች በገንዘብ መዋጀት ይኖርብሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ቍጥራቸው ከሌዋውያን ቍጥር በሁለት መቶ ሰባ ሦስት በልጦ የተገኘውን እስራኤላውያን በኵሮች ለመዋጀት፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ከሌዋውያን ወንዶች ቍጥር በላይ የሆኑትን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት የእስራኤል ልጆች በኵራትን ለመዋጀት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ስለ ተረ​ፉት ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ቤዛ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 በሌዋውያን ላይ ከእስራኤል ልጆች በኵር ስለ ተረፉት ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ቤዛ፥ በየራሱ አምስት ሰቅል ውሰድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 3:46
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአህያ የተወለደውን በኲር ግን የበግ ጠቦት በመተካት ከእግዚአብሔር እጅ ትዋጁታላችሁ፤ አህያውን ለመዋጀት ካልፈለጋችሁ ግን አንገቱን ስበሩት፤ በኲር የሆነውንም ወንድ ልጅ ሁሉ መዋጀት ይገባችኋል።


የግብጽ ንጉሥ ልቡን አደንድኖ እልኸኛ በመሆን አለቃችሁም ባለ ጊዜ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የሰውንም ሆነ የእንስሶችን በኲር ሁሉ ገደለ፤ በኲር ሆኖ የተወለደውን ወንድ እንስሳ መሥዋዕት አድርጌ የማቀርበው በዚህ ምክንያት ነው፤ በኲር ሆነው የተወለዱትን ወንዶች ልጆቻችንን ግን እንዋጃቸዋለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች